Sunday, 9 March 2014

በእንተ ቅዱሳት ሥዕላት- ስለ ቅዱሳት ሥዕላት-[ON THE SPIRITUALITY OF ICONS]


Icons have had a place in Christian worship as early as we can establish.
ጥያቄ አለኝ፡- የቅዱሳን ሥዕል ይናገራል ትላለህ?
ዘማርያም፡- እንዴታ!
ጥያቄ አለኝ፡-ግዕዛን የሌለው (መተንፈስ፣ማሰብ፣መናገር የማይችሉ) ሥዕል ይናገራል ማለት እንደምን ይመቻል; ሐሰት አይሆንም?
ዘማርያም፡- ዳዊት በሚጸልይበት ጊዜ "ሰማያት ይነግራ ስብሐተ እግዚአብሔር- ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፡፡" መዝ.181 ስለሚል ሰማያት በምን አፋቸው ይናገራሉ ትላለህ? አትልም፡፡
ጥያቄ አለኝ፡- እላለሁ እንጂ፡፡
ዘማርያም፡- ግዕዛን የሌላቸው ሰማያት የእግዚአብሔር ምስጋናን ይናገራሉ ማለት እንደምን ይመቻል ሐሰት አይሆንም?
ጥያቄ አለኝ፡- ያስ እንደ ስልቱ ይተረጎማል፤ በሰማያት ያሉ መላእክት እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ ተብሎ፡፡
ዘማርያም፡- ይህም እንደ ስልቱ ይተረጎማል፤ በሥዕሉ ያደረ አምላክ ይናገራል ተብሎ አድገ በለዓም(የበለዓም አህያ) እብነ ቢታንያን(የቢታንያን ድንጋዮችን) ያናገረ አምላክ ሥዕልን ማናገር ያቅተዋል? "ለእመ አርመሙ እሉ እሎንቱ አእባን ይኬልሑ- እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ" ሉቃ. 1940፡፡ ዳግመኛስ "ወተዛለፎ ለበለዓም በኃጢኣቱ ዘኢይነብብ አድግ በቃለ እጓለ እመሕያው- ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነቢዩ እብደት አገደ፡፡" 2.ጴጥ. 216 ተናገረ ብሏል፡፡ ነገር ግን ዘይቤውን ሸልቶ መሄድ ነው እንጂ የጠመመውን አቅንቶ የጎደለውን መልቶ መተርጎም የለም ብለህ ስታስተምር ኑረህ ዛሬ በጭንቅ እንደ ስልቱ ይተረጎማል ማለትህ ነገርህ ፈራሽ እንደሆነ በዚህ ይታወቃል፤ የለም ብሎ አለ የሚል መላላሽ ነውና፡፡
ጥያቄ አለኝ፡- ያስ ይሁን ሥዕል ሥራ ይሠራል ትላለህ?
ዘማርያም፡- እንዴታ!
ጥያቄ አለኝ፡- ሥራ ምንድር ነው?
ዘማርያም፡- ልጅ ያስወልዳል፤ ከብት ያረባል፡፡
ጥያቄ አለኝ፡- ሥዕል ልጅ ሊያስወልድ ከብት ሊያረባ እንደምን ይቻለዋል?
ዘማርያም፡- አባግዓ ያዕቆብን(የያዕቆብን በጎች) ተመልከት፤ የተሳለች ዝንጉርጉር በትርን እያዩ ሲወልዱ ሲረቡ እንደ ነበሩ፤ "ያዕቆብም ልብን ለውዝ ኤርሞን ከሚባሉ እንጨቶች እርጥብ በትርን ወስዶ በበትሮቹ ውስጥ ያለው ነጭ እንዲታይ ነጭ ሽመልመሌ አድርጎ ላጣቸው፡፡ የላጣቸውንም በትሮች በጎቹ ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ ውኃ ማጠጫውን ገንዳ ውስጥ በበጎቹ ፊት አኖራቸው በጎቹም ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ ይገAመጁ ነበር፡፡ በጎቹም በትሮቹን አይተው፤ ከመገAምጀታቸው የተነሣ ፀነሱ፤ በጎቹም ሽመልመሌ መሳይና ዝንጉርጉር ነቁጣም ያለበቱን ወለዱ፡፡" ዘፍ. 3037-39፡፡ በትሩን እየላጠ ዝንጉርጉርን አድርጎ በውኃው ሲያሳያው በጎቹ ዝንጉርጉርን በትር እያዩ ይወልዱ፣ ይረቡ ነበርና ሥዕለ በትር ከብትን ያረባ ሥዕለ ቅዱሳን እንደምን አይረባ!!!
ጥያቄ አለኝ፡- እውነት ነው እሱ "ለይኩን-ይሁን" ሲለው ይደረጋል!!
ዘማርያም፡- ሥዕለ ቅዱሳንም እሱ ለይኩን-ይሁን ሲለው ሁሉን ያደርጋል፡፡
ጥያቄ አለኝ፡- "ሰአሊ ለነ ሰንበተ ክርስቲያን- በቅዳሴ አትናቴዎስ ላይ ሰንበተ ክርስቲያን(ዕለተ እሑድን) ለምኝልን" ትላላችሁሳ!! 
ዘማርያም፡- እንዴታ!! እንላለን፡፡
ጥያቄ አለኝ፡- ግዕዛን(አዕምሮ) የሌላትን ዕለት ለምኚልን ማለት እንደምን ይመቻል; አዕምሮ ማጣት ያስመስል የለም?
ዘማርያም፡- ዳዊት በሚጸልይበት ጊዜ "ዕለት ለዕለት ትጎሥዕ ነቢበ፤ ወሌሊት ለሌሊት ታየድዕ ጥበበ- ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፤ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች፡፡" መዝ. 182 ትል የለምን? አዎን እላለሁ፡፡
ጥያቄ አለኝ፡- ግዕዛን(አዕምሮ) የሌላት ጥበብን ትናገራለች ማለት እንደምን ይመቻል; አዕምሮ ማጣት ያስመስል የለም?
ዘማርያም:- እንደ ስልቱ ይተረጎማል፤ "ሰአሊ ለነ ሰንበተ ክርስቲያን- ሰንበተ ክርስቲያን ዕለተ እሑድ ለምኝልን" ማለትም ዕረፍተ ክርስቲያን የፈጠርህ አምላክ መንፈሳዊ ዕረፍትን ስጠን ተብሎ፡፡ ምነው ጌታችንስ "ነገር ግን እላችኋለሁ፤ በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል፡፡" ማቴ. 1122 ሲል ጢሮስና ሲዶና ሲል በጢሮስና በሲዶና የሚኖሩ ሕዝቦችን እንጂ ሐገሩን ነውን; አይደለም!! ወዮልሽ ቅፍርናሆም! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ ሲልስ የቅፍርናሆምንና የቤተ ሳይዳ ሕዝቦችን ክፋትና አለማመን እንጂ መናገር መጋገር የማትችለውን ሐገርን ነውን; አይደለም!!!!
ጥያቄ አለኝ፡- እውነት እሱ!! ግን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እግዚአብሔር በቅዱሳት ሥዕላት ክብሩን የሚገልጽ አብነት ይገኛል?
ዘማርያም፡- እንዴታ!! ቸሩ ፈጣሪያችን ሕያው እግዚአብሔር ታቦትን እንዲሰራ ለነቢዩ ሙሴ ሲያዘው ሁለት የኪሩቤል ሥዕል እንደሚናተፉ አውራ ዶሮዎች አድርጎ እንዲስል ያዘዘ ነው፡፡ በዚህ ሥዕለ ኪሩቤል ላይ ሆኖም እግዚአብሔር ሙሴን ያናግረው አንደ ነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ በዚያውስ ላይ "የእግዚአብሔር ክብርም ከኪሩቤል ወጥቶ በቤቱ መድረክ ላይ ቆመ፤ ቤቱም በደመናው ተሞላ፤ አደባባዩም በእግዚአብሔር ክብር ፀዳል ተሞላ፡፡" ሕዝ. 104፡፡ ይል የለምን; ዳግመኛም "የእግዚአብሔርም ክብር ከቤቱ መድረክ ላይ ወጥቶ በኪሩቤል ላይ ቆመ፡፡ ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ዘረጉ፤ እኔም እያየሁ ከፍ ከፍ አሉ፤ በወጡም ጊዜ መንኮራኩሮች በአጠገባቸው ነበሩ፤ በእግዚአብሔርም ቤት በምሥራቁ በር መግቢያ ቆሙ፤ የእሥራኤልም አምላክ ክብር በላያቸው ላይ ነበረ፡፡" ሕዝ. 1018-19 እንዲል፡፡
ጥያቄ አለኝ፡- የቀደምት አበው መጻሕፍት በተለይም የውጭ አኃት አብያተ ክርስቲያናት አበው ስለ ቅዱሳት ሥዕል ምን ይላሉሳ;
ዘማርያም፡-St John of Damascus (ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ) wrote:
“Some people reprove us for honouring images of the Saviour, of the Mother of God
and other holy servants of Christ. But let them think for a moment.
In the beginning God created humanity in his own image. Why ever should we have
such respect for one another, if not because we are made in the image of God?
In Basil’s(
የባስልዮስ) words, ‘the honour paid to the image is in reality paid to its prototype,’ that
is to say, to what the image represents. Thus the Jewish people revered the
Tabernacle because that, much more than the rest of creation, was an image of God.
The making and the veneration of images are not a novelty. They are based on a very
ancient tradition.
St Ignatius, bishop of Antioch, (
ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ) made the comment:
“He who possesses in truth the word of
Jesus, can hear even its silence.”
Regarding the use of symbols in iconography, one of the church fathers explains:
“There are no words, nor lines which could represent the Kingdom of God, as we
represent and describe our world. Both theology and iconography are faced with a
problem, which is absolutely insoluble –to express by means belonging to the created
world, that which is infinitely above the creature. On this plane, there are no
successes, for the subject itself is beyond comprehension, and no matter how lofty in
content and beautiful an icon may be, it cannot be perfect, just as no word or image
can be perfect. In this sense both theology and iconography are failures. Precisely in
this failure lies the value of both alike; for this value results from the fact that both
theology and iconography reach the limit of human possibilities and prove
insufficient. Therefore the methods used by iconography for pointing to the Kingdom
of God, can only be figurative and symbolical, like the language of the parables in the
Holy Scriptures.”
In the Coptic Church, icons follow certain symbolism that carries a theological
message.
St Ambrose(
ቅዱስ አምብሮስ) writes of her:
“The life of Mary shines forth as from a mirror, all the beauty and chastity and the
pattern of every virtue.”
Thus, it is not surprising that St Jacob of Sarug(
ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ) expressed:
“How could I paint the picture of this marvellous, beautiful one with ordinary
colour? Too exalted and too glorious is the image of her beauty!”
Mary is found in many icons, most frequently holding Christ. And although the icons have numerous variations, she always has one hand which motions towards her son – the action that sums up her entire life to the present day.

Thus, in conclusion, icons in the Orthodox tradition are not to be taken as pieces of
artistic device, but rather, as windows or doors into spiritual world. They are designed
to enhance the spiritual life of the believer through emulating the virtues of the icon’s
prototype. And therefore, icons can be a blessing in our lives if we use them in a
spiritual way.
እግዚአብሔር ለኹላችንም ትሑት ስብእና ቅን ሕሊና አስተዋይ ልቡና ይስጠን፡፡ አሜን፡፡
ስምዓት(ምንጭ)- መጽሐፈ ጥበብ፤ ዘአስተጋብእዎ አኀው ማኅበረ ቢዘን፤ ገጽ.49-51.
- “THE SPIRITUALITY OF ICONS”, By His Grace Bishop Daniel


2 comments:

  1. kale hiwot yasemalin. betam astemari naw

    ReplyDelete
  2. ቃለ ህይወት ያሰማልን

    ReplyDelete