Thursday, 27 March 2014
የንስሐ አባት መያዝ ለምን ያስፈልጋል???
የንስሐ አባት መያዝ ለምን ያስፈልጋል???
· በወንጌል
“ ለወይን ስፍራዉ ሰራተኞችን ይቀጥር ዘንድ በማለዳ ወጣ በአስራ አንድ ሰአትም ቀጠረ”
የሚለዉ ምሳሌ፡ ማለዳ በተባለ የልጅነት እድሜ ላይ የሚጠብቅ የሚኮተኩት መምህረ ንስሃ መያዝ እንደሚያስፈልግ ያሳያል፡፡ዕድሜያችን ለሀጢአት በደረሰችበት ቅፅበት ለንስሃም(ለ ኑዛዜም) ትደርሳለችና፡፡
· በሲራክ
6-6 ላይ “ብዙ
ሰዎች ወዳጆች ይሁኑህ ከብዙዎች አንዱ ምክርህን የምትነግረው ከልቡናህ ጋር አንድ ይሁን፡፡”
የሚለው ቃል ምእምናን ስለ ሐይማኖትና ምግባር
የሚያስተምbቸው
ብዙ ካህናት ሊኖሩዋቸው ቢችሉም ከብዙዎች አንዱ ግን ንስሃቸውን የሚናዘዙለት መምህረ ንስሃ ሊሆናቸው እንደሚገባ ያጠይቃል፡፡
· አዳም
በገነት ለሰባት አመታት ከቆየ በሁዋላ በዲያቢሎስ
ተፈትኖ እንደወደቀ፡ በሃጢያት መፈተንና መዉደቅ ለሰው የሚፀናበት ዕድሜ ከሰባት
አመት ጀምሮ ስለሆነ ወደ
ንስሃ አባት መቅረብ ይኖርበታል፡፡
· በምክረ ካህን መኖር ራሱ ትልቅ መንፈሳዊ ማእረግ ነው የአዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች ከብሉይ ኪዳን ሰዎች የሚከብሩትን ያህል በምክረ ካህን የሚኖሩ ምእምናን ከአማኒያን በላይ የከበሩ ናቸዉ፡፡
ሀጢያትን
ለእግዚአብሄር በካህን በኩል መናዘዝ መፅሃፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያለዉ ጠቃሚ ጉዳይ ነዉ፡፡ እግዚአብሄር አዳም በበደለ ጊዜ “አዳም ሆይ ወዴት ነህ?” ብሎ የጠየቀዉ አዳም እንዲናዘዝ ስለፈለገ እንጂ አዳም ያደረገዉን ሳያዉቅ
ቀርቶ አልነበረም፡፡ “እምቅድመ ይፍጥሮ ለአዳም የአምር ግብሮ” ”አዳምን ከመፍጠሩ በፊት ስራዉን ያዉቃል” እንዲል፡፡ አዳምም እግዚአብሄር በጠየቀዉ ጊዜ ”ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ” በማለት ተናዝዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ቦታዎች ሰዎች ሀጢያታቸዉን ይናዘዙ እንደነበር በመፅሀፍ ቅዱስ ተገልÚል፡፡ ሐዋ 19-18 ፡ማቴ3 5-6 ፡ዘሌ 5-16፡ ኢያ 2- 19፡፡ ይሁን እንጂ “ሀጢያቴን ለመተዉ ከፈቀድኩ አይበቃም ወይ? መናዘዙ ለምን አስፈለገ?” የሚሉ ሰዎች አሉ ሀጢያትን በካህን ፊት መናዘዝ ግን የሚከተሉት ጠቀሜታዎች
አሉት፡-
v ሀጢያትን በዝርዝር በካህን ፊት መናዘዝ ዳግመኛ በዚያ ሀጢያት ላለመያዝ ሀይልን ይሰጣል፡፡ ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ “በበደሉ ላይ ድፍረትና
ሽንገላን የሚጨምር (ሀጢያት ሰርቶ እንዳልሰራ ዝም የሚል) ከዚያች ሀጢያት መጠበቅ አይችልም፡፡ እርስዋን በምትመስል ሀጢያት ከመዉደቅም
አይድንም” እንዳለ፡፡
v ንጉስ የሚሽረዉና የሚሾመዉን ግራና ቀኝ አቁሞ የሚሽረዉን
ወቅሶ የሚሾመዉን አሞግሶ እንደሚያከብር ያለፈ ሀጢያታችንን በካሀኑ ፊት ስንዘረዝርም ያለፈዉን ሀጢያታችንን ሽረን በሚመጣዉም
ህይወት ያንን ሀጢያት ላለመድገም እየወሰንን ነው፡፡
v ኑዛዜ ያሳቅቃል፡፡ መሳቀቁ ደግሞ ለሰራነዉ ሀጢያት ዋጋ ነዉ፡፡ በፍርድ ቀን ጌታ በሰማይ መላእክት ፊት ሀጢያታችንን ገልጦ
ከሚያሰቅቀን ይልቅ እኛዉ እራሳችን እዚሁ እንደኛዉ ደካማ ሰዉ በሆነው በካህኑ ፊት በመናዘዝ ለሰራነው እጅግ ግዙፍ ሃጢያት የምንቀበለው
ኢምንት ቅጣት ነው፡፡
v በሽታውን የደበቀ መድሃኒት የለውም እንደሚባለው የነፍሱን
ደዌ ሀጢያቱን የሚደብቅም እንዲሁ መፍትሄ አያገኝም፡፡ የካህኑን ፀሎትና
ምክርም ያጣል፡፡ “ሀጢያቱን የሚደብቅ /የሚሰውር አይለማም፡ የሚናዘዛትና የሚተዋት ግን ምህረትን ያገኛል” እንደተባለ ፡፡ምሳ8-13
ሀጢያታችንን ለምን በቀጥታ ለእግዚአብሄር ብቻ አንናዘዝም??
· ሀጢያትን ለካህን መናዘዝ ለእግዚአብሄር አለመናዘዝ አይደለም፡፡ ሀጢያትን ለካህን መንገር ለእግዚአብሄር መናዘዝና ክብር
መስጠት ነው፡፡ እያሱ እንዳለ “ልጄ ሆይ ለአምላክ ከብርን ስጥ፡ ለእርሱም ተናዘዝ፡ ያደረግከውንም ንገረኝ አትሸሽገኝ” ኢያሱ 7-19፡፡ ኢያሱ
“ክብርን ስጥ” ያለው ለእግዚአብሄር: “ተናገር” ያለው ግን ለራሱ መሆኑ ሀጢያትን ለካህን መናዘዝ ለእግዚአብሄር ክብር መስጠት እንደሆነ ያሳየናል፡፡ አበዉ ካሀናትም
ኑዛዜን ከተቀበሉ በ`ላ “እግዚአብሔር ይፍታህ” እንጂ ”ፈትቼሃለሁ ” አይሉም፡፡ ይህም ምንም
በነሱ ፊት ብንናገርም ሰሚዉም ሆነ በእነርሱ እጅ ስርየት የሚሰጠዉ እርሱ ባለቤቱ ስለሆነ ነው፡፡ ”ሁለት ወይም ሶስት በሚሆኑበት
በዚያ በመካከላችሁ እገኛለሁ” ብሎ ቃል የገባ አምላክ በአናዛዚው ካህንና በተናዛዚው
ምእምን መካከል ሆኖ ይሰማል፡ ስርየትንም ይሰጣል፡፡
· ሰው ሲታመም ሀኪም ቤት ሄዶ በሀኪሙ ፊት ”ቆረጠኝ ወጋኝ. . . ” እያለ ህመሙን እንደሚያብራራው ሁሉ፡ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ያሉት ካህናትም
የነፍስ ሀኪሞች ናቸውና እያንዳንዱን የነፍስ በሽታ (ሀጢያት) በዝርዝር በእነርሱ ፊት ልንናዘዝ ይገባል፡፡ በሀኪሙ ፊት ምንናዘዘው የእግዚአብሔርን ፈዋሽነት ክደን እንዳልሆነው ሁሉ በካህናት ፊት የምንናዘዘውም
የእግዚአብሔርን ሰሚነት ክደን አይደለም፡፡
· ለምን በቀጥታ ለእግዚአብሔር አልናዘዝም ማለት በራሱ ትዕቢት ነው፡፡ ንስሃ የሚገባ ሰው ሊል የሚገባው ”ከበደሌ ብዛት የተነሳ ቀና ብዬ የሰማይን ርዝመት አይ ዘንድ እንኩዋ አገባቤ አይደለም” ነው(ፀሎተ ምናሴ)፡፡
· በወንጌል እግዚአብሔር ”እርስ በርሳችሁ ሀጢያታችሁን ተናዝዙ” ያለው የሰው ልጅ ከፈጣሪ ይልቅ ሰውን ስለሚፈራና ስለሚያፍር
በሃጢያቱ እንዲሳቀቅ ስለፈለገ ነው፡፡ እግዚአብሔር ያየኛል ይሰማኛል ሳይል የሰራውን ሀጢያት እንዴት እግዚአብሔር
ያየኛል ይሰማኛል ብሎ ይናዘዛል? እነዚህ ከእግዚአብሔር ይልቅ ሰውን የሚፈሩትን መጽሐፍ እንዲህ ይላቸዋል ”እስመ ዐይነ ሰብእ ያፈርሆሙ
ወኢየአምሩ ከመ አይነ እግዚአብሔር ያበርህ እምእዕላፍ ፀሀይ” ”የሰው ዐይን ያስፈራቸዋል፡
የእግዚአብሔር አይን ግን ከብዙ አእላፍ ፀሀያት ይልቅ እንደሚያበራ አያውቁም!!!”
·
አንድ ምእመን ንስሃ በሚገባበት ጊዜ ሃጢያቱን ሳያድበሰብስ በዝርዝር ለካህኑ በሚገባ መልኩ መናዘዝ አለበት ፡፡ እንዳው በደፈናው “እኔ ያልሰራሁት ሃጢያት የለም ” ”አድርጉ ከተባለው ውስጥ ያደረግኩት አንድም መልካም ነገር የለም!” እያሉ የብልጠት
ኑዛዜ መናዘዝ አይገባም፡፡ አንድ በሽተኛ በሃኪም ፊት ”ታምሜአለሁ!
” ”በሽታ የተባለ ሁሉ አለብኝ!” በማለት መድሃኒት እንደማያገኝ ሁሉ ሃጢያቱን በዝርዝር እና በግልፅ ያልተናገረም በትክክል ስርየት አያገኝም
·
አንድ ምእመን ስለ ሃጢያቱ በግልፅ ሊናገር እና ሊዘረዝር ይገባል ሲባል ግን
በሆነው ባልሆነው ”እኔ ሃጢያተኛ ነኝ” ሊል ይገባል ማለት አይደለም፡፡ ”ድሃ ድህነቱን በአፉ
ይጠላታል” ሲራ 13-24 እንዳለ ”እንደኔ ሃጢያተኛ
ማን አለ?” እያሉ ሃጢያትን በአፍ መጥላት ገና ከሀጢያት ፍቅር ያለመላቀቅ ምልክት ነው፡፡ሃጢያትን የሚጠላት በንስሃ
ይርቃታልና፡፡ ሃጢያተኛ ነኝ እያሉ በማወጅ ንጹሃን ትሁታን የሚመስላቸው አሉ፡፡ ትሁታን ግን ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ እንዳለው ሃጢያተኛ ነኝ የሚሉት ሳይሆኑ ሃጢያተኛ ሲባሉ
የሚታገሱት ናቸው፡፡
·
በኑዛዜ ወቅት ትንኝን እያጠሩ ግመልን እንደመዋጥ ታላላቅ ሃጢያቶቻችንን ከጎን
ትተን ጥቃቅኑን ብቻ መናገር ስህተት ነው፡፡ ሲሰሩት ያልፈሩትን ሃጢያት ሲናገሩት መፍራት አይገባምና፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በአርጋኖን
ዘረቡዕ 7-5 እንዲህ እንዳለ ”ሃጢያቴን ለመናገር ለምን
አፍራለሁ? አለመናዘዜስ ለምንድን ነው? እኔ ሀጢያቴን ብሰውረው ሃጢያቴ ራሱ ሊከሰኝ ይጮሃል፡፡ እንኪያስ እንዳልበደለ ለምን
ዝም እላለሁ? የሰራሁትን ክፉ ስራዬ ያሳጣኛል እኔ እንዳልሰራ ለምን እሆናለሁ? የሚዘልፈኝ አልሻም፡ እኔ ራሴ ለራሴ የራሴን ዘለፋ አነባለሁ እንጂ”፡
·
በኑዛዜ ወቅት ለሀጢያት ምክንያት መደርደርና የሌሎችን ሀጢያት አክሎ መናገር
አይገባም ”እገሌ እንዲህ አድርጎ ስለገፋፋኝ እንዲህ አድርጌ ነበር” አያሉ
ሌላውን መክሰስና ምክንያት መስጠት ይቅር ሳይሉ ይቅርታ መሻት ነውና፡፡ ጌታችንም በወንጌል ”ከሳሾችሽ ወዴት አሉ?” ያላትን ሴት ”አኔም አልፈርድብሽም” ብሎ በይቅርታ ያሰናበታት
ስለ ከሳሾችዋ አንዳች ባለመናገሩዋ ነበር ዮሀ 8-11፡፡
·
ሰው ሆኖ የማይበድል እንጨት ሆኖ የማይጨስ የለምና እንዲሉ ሰው ሁልጊዜ ከበደል
ንጹህ ይሆን ዘንድ አይችልም በንስሃ ሃጢያቱን የሚናዘዝ ሰው ዳግመኛ አይበድልም
ማለት አይደለም፡፡ ከንስሃ በሁዋላ በሃጢያት ተፈትነን
ብንወድቅ ተስ”ፋ ሳንቆርጥ ወዲያው ንስሃ ልንገባ ይገባል ”መልሼ
ልበድል ለምን ንስሃ እገባለሁ” ማለት ግን ”መልሶ
ለሚርበኝ ለምን እበላለሁ” ”መልሼ ለምቆሽሽ ለምን
እታጠባለሁ” እንደ ማለት ነው ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ ”መውደቅ አዳማዊ ነው ወድቆ አለመነሳት ግን ዲያቢሎሳዊ ነው” እንዳለው ተሰፋ ቆርጦ
በንስሃ መነሳት ይኖርብናል እግዚአብሄር ይቅር ማለት ሳይሰለቸዉ
ሰው ይቅር በለኝ ማለት ሊሰለቸው አይገባም
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Kale Hiwote Yasemalene.
ReplyDeleteቃለ ሕይወት ያሰማልን
ReplyDeleteKale hiwot yasemalin des yemil kal new egziabher behaymanotk bemgbark yatsnak
ReplyDeleteKale hiwot yasemalin des yemil kal new egziabher behaymanotk bemgbark yatsnak
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማልን
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሠማልን
ReplyDeleteእግዚአብሄር ይስጥልኝ። ቃለ ህይወት ያሰማልኝ
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይስጥልኝ ቃለ ህይወት ያሰማልን በእውነት ትልቅ የነፍስ መንገድ ነው አስፈላጊም ነው
ReplyDeletekaryan
ReplyDeleteExcellent
ReplyDeleteቃለ ሒወት ያሠማልን
ReplyDeleteDownloade
ReplyDelete