Sunday, 9 March 2014

+++ አጋንንት የማጭበርበር ሥራ ይሠራሉ እንጂ ከቶ ትንቢት መናገር ወይም የሰውየውን ሃሳብ ማወቅ አይችሉም

+++ ብዙውን ጊዜ አጋንንት የሚገለጹበት አሠራር በሚያስፈራ መልክ ነው:: ንግግራቸው በትዕቢት የተሞላ ነው:: /ኢሳ.10:14/ በአብዛኛው ራሳቸውን እየለወጡ የማስመሰል ሥራ ይሠራሉ:: ባሕታውያን ሲተኙ ለጸሎት እየቀሰቀሱ እንቅልፍ ይነሣሉ; አንዳንዴም ለጾም ያደሉ በማስመሰል ምንም እንዳንመገብ ይመክሩናል:: ለጸሎት በሚተጋ መነኩሴ አምሳል ይገለጣሉ:: ይህንን ሁሉ የሚያደርጉት ሰዎች ለጊዜው ከአቅም በላይ በመትጋት በሗላ ግን እንዲሰለቹና ተዳክመው ተስፋ እንዲቆርጡ የብሕትውና ኑሮ ሸክም የበዛበትና የማይቻል ነው በሚል ሃሳብ እንዲያቁዋርጡት ለማድረግ ነው:: አጋንንት የማስመሰልና የማስፈራራት ሥራ የሚያበዙት በእውነት የሚያሸንፉበትን ኃይላቸውን ስላጡና ዲያብሎስ በጌታችን የማዳን ሥራ ስለ ወደቀ ነው:: በተጨማሪም አጋንንት ትንቢት መናገር የሚችሉ ወይም ሃሳባችንን ሳንገልጸው በፊት ማወቅ የሚቻላቸው መስለው ይቀርባሉ:: ለምሳሌ አንድ ወንድም ወደኛ ለመምጣት አስቦ መንገድ ሲጀምር አጋንንት መንፈስ ስለሆኑ ቀድመው ይደርሱና 'እከሌ ይመጣል' ብለው ይናገራሉ:: እኛም ሰውየው ሲመጣ በእውነት ትንቢት የተነገረ ስለ ሚመስለን እንደነቃለን:: በዚህ ዘዴ አጋንንት የማጭበርበር ሥራ ይሠራሉ እንጂ ከቶ ትንቢት መናገር ወይም የሰውየውን ሃሳብ ማወቅ አይችሉም::[የበረሓው ኮከብ- ቅዱስ እንጦንስ; ዘደረሰ ቅዱስ አትናቴዎስ]

No comments:

Post a Comment