Sunday, 9 March 2014

ለማይፈጽመው ሰው ትምህርት መጀመር እፍረት ነው፡፡



"ላልተማረ ሰው መጻሕፍትን ማስተማር አፍረት ነው፤ ለስልብ ሰው ከድንግል ጋር መተኛት አፍረት ነው፤ ጡት ለሌላት ሴት ሕፃን ማሳደግ እፍረት ነው፤ እንጀራ ሳይኖር ማዕድ ማዘጋጀት እፍረት ነው፤ ለተጠሙ ሰዎች የደረቁ ወንዞችን መጎብኘት እፍረት ነው፤ ፊደሎችን ለማያውቅ መጻሕፍትን መግለጽ እፍረት ነው፤ የቅኝቱን ምት ለማይችሉ መሰንቆ መያዝ እፍረት ነው፤ ለአራሽ ጦር መወርወር፤ ፈረስ መጋለብም እፍረት ነው፤ ለችግረኛ የማያገኘውን መለመን የሚያሳፍር ነው፤ በዘፈን ጨዋታ መካከል ልቅሶ የሚያሳፍር ነው፡፡ በሚያለቅሱ ሰዎች መካከል በልብስ ማጌጥ እፍረት ነው፤ ለማይፈጽመው ሰው ትምህርት መጀመር እፍረት ነው፡፡"[ መጽሐፈ ምሥጢር፣ የፋሲካ ማክሰኞ ምንባብ፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ]

No comments:

Post a Comment