Wednesday, 5 March 2014

+ ዳዊት ደጋሚ ትውልድ እንዳይጠፋ ዳዊት ደጋሚ እንሁን::

+ በዚህ ዓብይ ጾም ወቅት ሁሉም ማኅበረ ምዕመናን ወምዕመናት የሚነበቡትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶች በቅድሚያ አውቀው; ምስባኩን; ቅዳሴውን ከግጻዌ(Lectionary) አይተው ቢያስቀድሱ ይመረጣል:: ጾም ከጸሎት ጋር ያማረ ነውና ውዳሴ ማርያም; መዝሙረ ዳዊት መደገም(መጸለይ) ይገባል:: የበረታም ውዳሴ አምላክ; መልክአትን ወዘተ... ጸሎታትን ሊጸልይ ይገባል:: መዝሙረ ዳዊት; * ሰኞ የሚጸለየው(ዘሰኑይ). 1).ፍካሬ ከመዝ.1 እስከ መዝ.10. 2).አድኅነኒ ከመዝ.11 እስከ መዝ.20. 3). አምላኪየ ከመዝ.21 እስከ መዝ.30. ነው:: *ዘሠሉስ(የማክሰኞ); 1).ብፁዓን ከመዝ.31 መዝ 40. 2). ከመ ያፈቅር ከመዝ.41- መዝ.50. 3). ለምንት ይዜኃር ከመዝ.51- መዝ.60. ድረስ ነው:: *ዘረቡዕ; 1).አኮኑ መዝ.61 እስከ መዝ.70. 2). እግዚኦ ኩነኔከ; ከመዝ.71 እስከ መዝ 80 ድረስ ነው:: *ዘሐሙስ; 1).እግዚአብሔር ቆመ; ከመዝ.81- መዝ.90. 2).ይኄይስ ከመዝ.91- መዝ.100. 3).ስምዐኒ; ከመዝ.101-መዝ.110 ድረስ ያለው ነው:: *ዘአርብ; 1).ብፁዕ ብእሲ ከመዝ.111-መዝ.120. 2).ተፈሣሕኩ; ከመዝ.121- መዝ.130 ድረስ ያለው ነው:: *ዘቀዳሚት ሰንበት(የቅዳሜ) 1).ተዘከሮ ከመዝ.131-መዝ.140. 2).ቃልየ ከመዝ.141- መዝ.150. 3).ሰሎሞን(መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን) 5:: N.B. መኀልይ በወርኃ ጽጌ የሚባል አለ:: *ዘሰንበተ ክርስቲያን(የእሁድ) ነቢያት; ብዛታቸው 15 ናቸው:: ስለሆነም ዳዊት ስንደግም እንደ ውዳሴ ማርያም ሊቃውንት የየዕለቱን አሰናድተውልናልና ጸልየን ከጸሎታችን ተጠቃሚ ያድርገን:: ዳዊት ደጋሚ ትውልድ እንዳይጠፋ ዳዊት ደጋሚ እንሁን::

3 comments:

  1. ዘማርያም ዘለቀ5 March 2014 at 22:13

    የእግዚአብሔር ቃልን ያድምጡ፤ ይገዙለትም፡፡

    ReplyDelete
  2. እግዚአብሔር ይስጥልን

    ReplyDelete
  3. መኀልየ መኀልየ ዘሰለሞን ዘወርኀ ፅጌ ሁሌ ይደገማል አይደገመም ነው ወይስ በወርኀ ፅጌ ብቻ ነው የሚደገመው

    ReplyDelete