Wednesday, 5 March 2014

የውሻ የትግል ጩኸት ለጅብ እንጂ ለአይጥ አይጠቅምም:: ለአይጥ የድመት እንጂ የውሻ ጩኸት አያስደነግጣትም

+ ውሻ ለጅብ የሚጮኸው ጩኸት በደጅ ላይ ያለ ጅብን እንጂ ቤት ውስጥ ምትርመጠመጠው እንቅልፍ እየነሳች; ንብረት ምታወድመውን አይጥን አያስደነግጣትም:: የውሻ የትግል ጩኸት ለጅብ እንጂ ለአይጥ አይጠቅምም:: ለአይጥ የድመት እንጂ የውሻ ጩኸት አያስደነግጣትም:: ስለሆነም በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ተሰግረው ያሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮች በአንድ አቅጣጫ ጩኸት ብቻ መፍትሔት አያገኙም:: ለመናፍቃን ተቃውሞ የምንጨኸው ጩኸት; በመቅደሱ ያሉ ኢ-ክርስቲያናዊ የሆኑ ዘረኞችን አያስደነግጥም:: ጉቦ ለሚቀበሉ; ገንዘብ የሚዘርፉ አገልጋዮችን በመቃወም ብንጮኽ; ይህ ጩኸት ዘረኞቹንም; የተሐድሶ መናፍቃንንም አያስደነግጥም:: ስለዚህ ለእያንዳንዱ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ችግር ተገቢ የሆነ ጩኸት(ድምጽ) በተገቢው ቦታና ሰዓት ማሰማት አለበን:: ሁላችንም ክርስቶሳውያን ስለእምነታችን ያገባናል:: ለቤተ ክርስቲያን ዘብ ለመቆም ቄስ; ዲ/ን መሆን አይጠበቅብንም:: ንጹሕ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጅ መሆናችን ይበቃል:: አንተ; እኔ; አንቺ; እናንተ; እናንቺ(ለሴቶች); እነሱም ሁላችንም ስለ ቤተ ክርስቲያን እኩል ያገባናል:: ደረጃችንና አቅማችንን ያገናዘበ ውግንና አምላከ ቅዱሳን አምላካችን እግዚአብሔር ለሁላችን ያድለን; አሜን::

No comments:

Post a Comment