+ በዚህ
ዓብይ ጾም ወቅት ሁሉም ማኅበረ ምዕመናን ወምዕመናት የሚነበቡትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶች በቅድሚያ አውቀው;
ምስባኩን; ቅዳሴውን ከግጻዌ(Lectionary) አይተው ቢያስቀድሱ ይመረጣል:: ጾም ከጸሎት ጋር ያማረ ነውና ውዳሴ
ማርያም; መዝሙረ ዳዊት መደገም(መጸለይ) ይገባል:: የበረታም ውዳሴ አምላክ; መልክአትን ወዘተ... ጸሎታትን
ሊጸልይ ይገባል:: መዝሙረ ዳዊት; * ሰኞ የሚጸለየው(ዘሰኑይ). 1).ፍካሬ ከመዝ.1 እስከ መዝ.10.
2).አድኅነኒ ከመዝ.11 እስከ መዝ.20. 3). አምላኪየ ከመዝ.21 እስከ መዝ.30. ነው::
*ዘሠሉስ(የማክሰኞ); 1).ብፁዓን ከመዝ.31 መዝ 40. 2). ከመ ያፈቅር ከመዝ.41-
መዝ.50. 3). ለምንት ይዜኃር ከመዝ.51- መዝ.60. ድረስ ነው:: *ዘረቡዕ; 1).አኮኑ መዝ.61
እስከ መዝ.70. 2). እግዚኦ ኩነኔከ; ከመዝ.71 እስከ መዝ 80 ድረስ ነው:: *ዘሐሙስ; 1).እግዚአብሔር
ቆመ; ከመዝ.81- መዝ.90. 2).ይኄይስ ከመዝ.91- መዝ.100. 3).ስምዐኒ; ከመዝ.101-መዝ.110
ድረስ ያለው ነው:: *ዘአርብ; 1).ብፁዕ ብእሲ ከመዝ.111-መዝ.120. 2).ተፈሣሕኩ;
ከመዝ.121- መዝ.130 ድረስ ያለው ነው:: *ዘቀዳሚት ሰንበት(የቅዳሜ) 1).ተዘከሮ ከመዝ.131-መዝ.140.
2).ቃልየ ከመዝ.141- መዝ.150. 3).ሰሎሞን(መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን) 5:: N.B. መኀልይ
በወርኃ ጽጌ የሚባል አለ:: *ዘሰንበተ ክርስቲያን(የእሁድ) ነቢያት; ብዛታቸው 15 ናቸው:: ስለሆነም ዳዊት
ስንደግም እንደ ውዳሴ ማርያም ሊቃውንት የየዕለቱን አሰናድተውልናልና ጸልየን ከጸሎታችን ተጠቃሚ ያድርገን:: ዳዊት
ደጋሚ ትውልድ እንዳይጠፋ ዳዊት ደጋሚ እንሁን::
የእግዚአብሔር ቃልን ያድምጡ፤ ይገዙለትም፡፡
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይስጥልን
ReplyDeleteመኀልየ መኀልየ ዘሰለሞን ዘወርኀ ፅጌ ሁሌ ይደገማል አይደገመም ነው ወይስ በወርኀ ፅጌ ብቻ ነው የሚደገመው
ReplyDelete