+
ሴቲቱ በሕርስ(ሐራስነት)
ና በትክት(በወር
አበባ) ውስጥ እያለች
ባልና ሚስት ሩካቤ
መፈጸም አይፈቀድላቸውም:: ምክንያቱም
በነዚህ ወቅቶች የሚፈጸም
ሩካቤ የሚወለደውን ሕጻን
ጨምሮ የባልና የሚስቱን
ጤና ሊጎዳ እንደሚችል
የሃይማኖት መጻሕፍቶቻችን ያውጃሉ::
ይህን የጤና መቃወስ
ብንተወው እንኩዋ በነዚህ
ዕለታት የሚፈጸም ሩካቤ
አስነዋሪና ስሜት አልባ
ስለሚሆን ስለራሳችን ሕሊና
ብለን ልንተወው ይገባናል::
የሰው ልጅ ዘር
ክቡር ነው:: ሴት
ልጅ በትክት(በወር
አበባ) ላይ ሳለች
ሩካቤን መፈጸም ክቡር
ዘርን እዳሪ ከሆነ
ደም ጋር መቀላቀል
ነውና ትልቅ ኃጢአት
ነው:: በሕርስ(ሐራስ
ሳለች) ጊዜ ደግሞ
ለብዙ ወራት ለመውለድ
ይዘጋጁ የነበሩ
ሕዋሳቶቿ ወደ ቀደመ ይዞታቸው ተመልሰው ሩካቤን ለመፈጸም ዝግጁ አያደርጉዋትምና በዚህ ጊዜ ውስጥ የሚፈጸም ሩካቤ የሁለቱንም ስሜት የሚጎዳ ነው:: ንጉሥ ዳዊት ከሰው ሚስት ጋር በመፈጸሙ ድርጊቱ ቢነቀፍም ከኦርዮ ሚስት ከቤርሳቤህ ጋር በምንጣፍ በተገናኘ ጊዜ ከወር አበባዋ ነጽታ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ሲጠቅስ "ዳዊትም መልእክተኞችን ልኮ አስመጣት ወደ እርሱም ገባች ከርኩሰትዋም ነጽታ ነበርና ከእርሷዋ ጋር ተኛ ወደቤቷም ተመለሰች ሴቲቱም አረገዘች:: 2ኛ.ሳሙ.11:4 "ከርኩሰትዋም ነጽታ ነበር" ያለው የወር አበባዋን ነበር:: ስለምን ቢሉ ደመ ትክቶ(የወር አበባ) በኦሪት የእርግማን ምልክት ነበርና:: ዘፍ.3:16:: መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ዓይነት አገላለጽ ቤርሳቤህ ከዳዊት ጋር የተገናኘችበትን ጊዜ መግለጽ የፈለገው ሴቶች ከወር አበባ በነጹበት ጊዜ ከወንድ ጋር ቢገናኙ ወዲያው ፅንስ ይይዛሉና በአንድ ጊዜ ፀነሰች ብሎ ለማስከተል ሲሆን በተጨማሪም ሩካቤ ከወር አበባ ጊዜ ውጭ የሚፈጸም እንደሆነ ለማስገንዘብ ነው:: መጽሐፍ ቅዱስ ሴት ልጅ በትክት(በወር አበባ) ላይ እያለች የሚፈጸም ሩካቤን ሲከለክል "እርሷም በመርገምዋ ርኩሰት ሳለች ኃፍረተ ሥጋዋን ትገልጽ ዘንድ ወደ ሴት አትቅረብ::" ዘሌ.18:19:: ይህንን ሕግ ተላልፎ ኃጢአት የሠራ ሰው ስለሚገባው ቅጣት ሲናገር ደግሞ "ማንኛውም ሰው ከባለ መርገም ሴት ጋር ቢተኛ ኃፍረተ ሥጋዋንም ቢገልጥ; ፈሳሽዋንም ገልጧልና እርሷም የደምዋን ፈሳሽ ገልጣለችና ሁለቱም ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ::" ዘሌ.20:18 ይላል::
Kale Hiwote Yasemalene!
ReplyDelete