Thursday, 27 March 2014
የንስሐ አባት መያዝ ለምን ያስፈልጋል???
የንስሐ አባት መያዝ ለምን ያስፈልጋል???
· በወንጌል
“ ለወይን ስፍራዉ ሰራተኞችን ይቀጥር ዘንድ በማለዳ ወጣ በአስራ አንድ ሰአትም ቀጠረ”
የሚለዉ ምሳሌ፡ ማለዳ በተባለ የልጅነት እድሜ ላይ የሚጠብቅ የሚኮተኩት መምህረ ንስሃ መያዝ እንደሚያስፈልግ ያሳያል፡፡ዕድሜያችን ለሀጢአት በደረሰችበት ቅፅበት ለንስሃም(ለ ኑዛዜም) ትደርሳለችና፡፡
· በሲራክ
6-6 ላይ “ብዙ
ሰዎች ወዳጆች ይሁኑህ ከብዙዎች አንዱ ምክርህን የምትነግረው ከልቡናህ ጋር አንድ ይሁን፡፡”
የሚለው ቃል ምእምናን ስለ ሐይማኖትና ምግባር
የሚያስተምbቸው
ብዙ ካህናት ሊኖሩዋቸው ቢችሉም ከብዙዎች አንዱ ግን ንስሃቸውን የሚናዘዙለት መምህረ ንስሃ ሊሆናቸው እንደሚገባ ያጠይቃል፡፡
· አዳም
በገነት ለሰባት አመታት ከቆየ በሁዋላ በዲያቢሎስ
ተፈትኖ እንደወደቀ፡ በሃጢያት መፈተንና መዉደቅ ለሰው የሚፀናበት ዕድሜ ከሰባት
አመት ጀምሮ ስለሆነ ወደ
ንስሃ አባት መቅረብ ይኖርበታል፡፡
· በምክረ ካህን መኖር ራሱ ትልቅ መንፈሳዊ ማእረግ ነው የአዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች ከብሉይ ኪዳን ሰዎች የሚከብሩትን ያህል በምክረ ካህን የሚኖሩ ምእምናን ከአማኒያን በላይ የከበሩ ናቸዉ፡፡
ሀጢያትን
ለእግዚአብሄር በካህን በኩል መናዘዝ መፅሃፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያለዉ ጠቃሚ ጉዳይ ነዉ፡፡ እግዚአብሄር አዳም በበደለ ጊዜ “አዳም ሆይ ወዴት ነህ?” ብሎ የጠየቀዉ አዳም እንዲናዘዝ ስለፈለገ እንጂ አዳም ያደረገዉን ሳያዉቅ
ቀርቶ አልነበረም፡፡ “እምቅድመ ይፍጥሮ ለአዳም የአምር ግብሮ” ”አዳምን ከመፍጠሩ በፊት ስራዉን ያዉቃል” እንዲል፡፡ አዳምም እግዚአብሄር በጠየቀዉ ጊዜ ”ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ” በማለት ተናዝዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ቦታዎች ሰዎች ሀጢያታቸዉን ይናዘዙ እንደነበር በመፅሀፍ ቅዱስ ተገልÚል፡፡ ሐዋ 19-18 ፡ማቴ3 5-6 ፡ዘሌ 5-16፡ ኢያ 2- 19፡፡ ይሁን እንጂ “ሀጢያቴን ለመተዉ ከፈቀድኩ አይበቃም ወይ? መናዘዙ ለምን አስፈለገ?” የሚሉ ሰዎች አሉ ሀጢያትን በካህን ፊት መናዘዝ ግን የሚከተሉት ጠቀሜታዎች
አሉት፡-
v ሀጢያትን በዝርዝር በካህን ፊት መናዘዝ ዳግመኛ በዚያ ሀጢያት ላለመያዝ ሀይልን ይሰጣል፡፡ ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ “በበደሉ ላይ ድፍረትና
ሽንገላን የሚጨምር (ሀጢያት ሰርቶ እንዳልሰራ ዝም የሚል) ከዚያች ሀጢያት መጠበቅ አይችልም፡፡ እርስዋን በምትመስል ሀጢያት ከመዉደቅም
አይድንም” እንዳለ፡፡
v ንጉስ የሚሽረዉና የሚሾመዉን ግራና ቀኝ አቁሞ የሚሽረዉን
ወቅሶ የሚሾመዉን አሞግሶ እንደሚያከብር ያለፈ ሀጢያታችንን በካሀኑ ፊት ስንዘረዝርም ያለፈዉን ሀጢያታችንን ሽረን በሚመጣዉም
ህይወት ያንን ሀጢያት ላለመድገም እየወሰንን ነው፡፡
v ኑዛዜ ያሳቅቃል፡፡ መሳቀቁ ደግሞ ለሰራነዉ ሀጢያት ዋጋ ነዉ፡፡ በፍርድ ቀን ጌታ በሰማይ መላእክት ፊት ሀጢያታችንን ገልጦ
ከሚያሰቅቀን ይልቅ እኛዉ እራሳችን እዚሁ እንደኛዉ ደካማ ሰዉ በሆነው በካህኑ ፊት በመናዘዝ ለሰራነው እጅግ ግዙፍ ሃጢያት የምንቀበለው
ኢምንት ቅጣት ነው፡፡
v በሽታውን የደበቀ መድሃኒት የለውም እንደሚባለው የነፍሱን
ደዌ ሀጢያቱን የሚደብቅም እንዲሁ መፍትሄ አያገኝም፡፡ የካህኑን ፀሎትና
ምክርም ያጣል፡፡ “ሀጢያቱን የሚደብቅ /የሚሰውር አይለማም፡ የሚናዘዛትና የሚተዋት ግን ምህረትን ያገኛል” እንደተባለ ፡፡ምሳ8-13
ሀጢያታችንን ለምን በቀጥታ ለእግዚአብሄር ብቻ አንናዘዝም??
· ሀጢያትን ለካህን መናዘዝ ለእግዚአብሄር አለመናዘዝ አይደለም፡፡ ሀጢያትን ለካህን መንገር ለእግዚአብሄር መናዘዝና ክብር
መስጠት ነው፡፡ እያሱ እንዳለ “ልጄ ሆይ ለአምላክ ከብርን ስጥ፡ ለእርሱም ተናዘዝ፡ ያደረግከውንም ንገረኝ አትሸሽገኝ” ኢያሱ 7-19፡፡ ኢያሱ
“ክብርን ስጥ” ያለው ለእግዚአብሄር: “ተናገር” ያለው ግን ለራሱ መሆኑ ሀጢያትን ለካህን መናዘዝ ለእግዚአብሄር ክብር መስጠት እንደሆነ ያሳየናል፡፡ አበዉ ካሀናትም
ኑዛዜን ከተቀበሉ በ`ላ “እግዚአብሔር ይፍታህ” እንጂ ”ፈትቼሃለሁ ” አይሉም፡፡ ይህም ምንም
በነሱ ፊት ብንናገርም ሰሚዉም ሆነ በእነርሱ እጅ ስርየት የሚሰጠዉ እርሱ ባለቤቱ ስለሆነ ነው፡፡ ”ሁለት ወይም ሶስት በሚሆኑበት
በዚያ በመካከላችሁ እገኛለሁ” ብሎ ቃል የገባ አምላክ በአናዛዚው ካህንና በተናዛዚው
ምእምን መካከል ሆኖ ይሰማል፡ ስርየትንም ይሰጣል፡፡
· ሰው ሲታመም ሀኪም ቤት ሄዶ በሀኪሙ ፊት ”ቆረጠኝ ወጋኝ. . . ” እያለ ህመሙን እንደሚያብራራው ሁሉ፡ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ያሉት ካህናትም
የነፍስ ሀኪሞች ናቸውና እያንዳንዱን የነፍስ በሽታ (ሀጢያት) በዝርዝር በእነርሱ ፊት ልንናዘዝ ይገባል፡፡ በሀኪሙ ፊት ምንናዘዘው የእግዚአብሔርን ፈዋሽነት ክደን እንዳልሆነው ሁሉ በካህናት ፊት የምንናዘዘውም
የእግዚአብሔርን ሰሚነት ክደን አይደለም፡፡
· ለምን በቀጥታ ለእግዚአብሔር አልናዘዝም ማለት በራሱ ትዕቢት ነው፡፡ ንስሃ የሚገባ ሰው ሊል የሚገባው ”ከበደሌ ብዛት የተነሳ ቀና ብዬ የሰማይን ርዝመት አይ ዘንድ እንኩዋ አገባቤ አይደለም” ነው(ፀሎተ ምናሴ)፡፡
· በወንጌል እግዚአብሔር ”እርስ በርሳችሁ ሀጢያታችሁን ተናዝዙ” ያለው የሰው ልጅ ከፈጣሪ ይልቅ ሰውን ስለሚፈራና ስለሚያፍር
በሃጢያቱ እንዲሳቀቅ ስለፈለገ ነው፡፡ እግዚአብሔር ያየኛል ይሰማኛል ሳይል የሰራውን ሀጢያት እንዴት እግዚአብሔር
ያየኛል ይሰማኛል ብሎ ይናዘዛል? እነዚህ ከእግዚአብሔር ይልቅ ሰውን የሚፈሩትን መጽሐፍ እንዲህ ይላቸዋል ”እስመ ዐይነ ሰብእ ያፈርሆሙ
ወኢየአምሩ ከመ አይነ እግዚአብሔር ያበርህ እምእዕላፍ ፀሀይ” ”የሰው ዐይን ያስፈራቸዋል፡
የእግዚአብሔር አይን ግን ከብዙ አእላፍ ፀሀያት ይልቅ እንደሚያበራ አያውቁም!!!”
·
አንድ ምእመን ንስሃ በሚገባበት ጊዜ ሃጢያቱን ሳያድበሰብስ በዝርዝር ለካህኑ በሚገባ መልኩ መናዘዝ አለበት ፡፡ እንዳው በደፈናው “እኔ ያልሰራሁት ሃጢያት የለም ” ”አድርጉ ከተባለው ውስጥ ያደረግኩት አንድም መልካም ነገር የለም!” እያሉ የብልጠት
ኑዛዜ መናዘዝ አይገባም፡፡ አንድ በሽተኛ በሃኪም ፊት ”ታምሜአለሁ!
” ”በሽታ የተባለ ሁሉ አለብኝ!” በማለት መድሃኒት እንደማያገኝ ሁሉ ሃጢያቱን በዝርዝር እና በግልፅ ያልተናገረም በትክክል ስርየት አያገኝም
·
አንድ ምእመን ስለ ሃጢያቱ በግልፅ ሊናገር እና ሊዘረዝር ይገባል ሲባል ግን
በሆነው ባልሆነው ”እኔ ሃጢያተኛ ነኝ” ሊል ይገባል ማለት አይደለም፡፡ ”ድሃ ድህነቱን በአፉ
ይጠላታል” ሲራ 13-24 እንዳለ ”እንደኔ ሃጢያተኛ
ማን አለ?” እያሉ ሃጢያትን በአፍ መጥላት ገና ከሀጢያት ፍቅር ያለመላቀቅ ምልክት ነው፡፡ሃጢያትን የሚጠላት በንስሃ
ይርቃታልና፡፡ ሃጢያተኛ ነኝ እያሉ በማወጅ ንጹሃን ትሁታን የሚመስላቸው አሉ፡፡ ትሁታን ግን ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ እንዳለው ሃጢያተኛ ነኝ የሚሉት ሳይሆኑ ሃጢያተኛ ሲባሉ
የሚታገሱት ናቸው፡፡
·
በኑዛዜ ወቅት ትንኝን እያጠሩ ግመልን እንደመዋጥ ታላላቅ ሃጢያቶቻችንን ከጎን
ትተን ጥቃቅኑን ብቻ መናገር ስህተት ነው፡፡ ሲሰሩት ያልፈሩትን ሃጢያት ሲናገሩት መፍራት አይገባምና፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በአርጋኖን
ዘረቡዕ 7-5 እንዲህ እንዳለ ”ሃጢያቴን ለመናገር ለምን
አፍራለሁ? አለመናዘዜስ ለምንድን ነው? እኔ ሀጢያቴን ብሰውረው ሃጢያቴ ራሱ ሊከሰኝ ይጮሃል፡፡ እንኪያስ እንዳልበደለ ለምን
ዝም እላለሁ? የሰራሁትን ክፉ ስራዬ ያሳጣኛል እኔ እንዳልሰራ ለምን እሆናለሁ? የሚዘልፈኝ አልሻም፡ እኔ ራሴ ለራሴ የራሴን ዘለፋ አነባለሁ እንጂ”፡
·
በኑዛዜ ወቅት ለሀጢያት ምክንያት መደርደርና የሌሎችን ሀጢያት አክሎ መናገር
አይገባም ”እገሌ እንዲህ አድርጎ ስለገፋፋኝ እንዲህ አድርጌ ነበር” አያሉ
ሌላውን መክሰስና ምክንያት መስጠት ይቅር ሳይሉ ይቅርታ መሻት ነውና፡፡ ጌታችንም በወንጌል ”ከሳሾችሽ ወዴት አሉ?” ያላትን ሴት ”አኔም አልፈርድብሽም” ብሎ በይቅርታ ያሰናበታት
ስለ ከሳሾችዋ አንዳች ባለመናገሩዋ ነበር ዮሀ 8-11፡፡
·
ሰው ሆኖ የማይበድል እንጨት ሆኖ የማይጨስ የለምና እንዲሉ ሰው ሁልጊዜ ከበደል
ንጹህ ይሆን ዘንድ አይችልም በንስሃ ሃጢያቱን የሚናዘዝ ሰው ዳግመኛ አይበድልም
ማለት አይደለም፡፡ ከንስሃ በሁዋላ በሃጢያት ተፈትነን
ብንወድቅ ተስ”ፋ ሳንቆርጥ ወዲያው ንስሃ ልንገባ ይገባል ”መልሼ
ልበድል ለምን ንስሃ እገባለሁ” ማለት ግን ”መልሶ
ለሚርበኝ ለምን እበላለሁ” ”መልሼ ለምቆሽሽ ለምን
እታጠባለሁ” እንደ ማለት ነው ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ ”መውደቅ አዳማዊ ነው ወድቆ አለመነሳት ግን ዲያቢሎሳዊ ነው” እንዳለው ተሰፋ ቆርጦ
በንስሃ መነሳት ይኖርብናል እግዚአብሄር ይቅር ማለት ሳይሰለቸዉ
ሰው ይቅር በለኝ ማለት ሊሰለቸው አይገባም
Monday, 24 March 2014
በጎቹና ፍየሎቹ
የሚከተለውን ምንባብ በጥንቃቄ አንብቡ
በጎቹና ፍየሎቹ
(በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ....ምንጭ፡ሐመር የካቲት 2003 ዓ.ም. )
ከዕለታት በአንዱ ቀን በአንድ ሀገር ትልቅ የበጎች በረት ነበረ፡፡ በዚህ የበጎች በረት ውስጥ ብዙ በጎች ይኖሩ ነበር፡፡ ይህ የበጎች በረት ለረዥም ዓመት የቆየ እና ብዙ ታሪክ ያለው በረት ሲሆን በጎቹ ሁሉ ግን የሚኖሩበትን በረት ጥንታዊነት እና ታሪክ በሚገባ የሚያውቁ አይደሉም፡፡ በቅርብ ጊዜ ከሚወለዱት በጎች መካከል ለመስማት ፈቃደኞች ያልሆኑ አሉ እንጂ በረቱን እስከ ዛሬ ድረስ ጠብቆ ለማቆየት ብዙ በጎች ከሚያገሳ አንበሳ ጋር ጭምር ተታግለው ብዙ ድል አድርገዋል፡፡ ብዙ በጎችም ለዚሁ በረት መቆየት ሲሉ አንገታቸውን እስከመስጠት ድረስ ደርሰው ነበር፡፡ ከአሁኑ በጎች ውስጥ ግን አንዳንዶቹ እንኳን ራሳቸውን መሥዋዕት አድርገው ሊሰጡ የቀድሞዎቹ በጎች የፈጸሙትን ገድል እንኳን ለማመን ይከብዳቸዋል ፤ ለመስማትም ይሰለቻሉ፡፡
በዚህ በረት ውስጥ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ አንድ ችግር ተፈጥሯል፡፡ የችግሩ መነሻ አንዳንድ ፍየሎች በጎች መስለው ከመንጋው መቀላቀላቸው ነው፡፡ እነዚህ ፍየሎች ምንም እንኳን ሥራቸው ፣ ድምፃቸው ፣ አኗኗራቸው ሁሉ ፍየል መሆናቸውን የሚመሰክር ቢሆንም ከበጎቹ በረት ረዥም ጊዜ የቆዩ በመሆናቸው ብዙ በጎችን ግራ ያጋባ ነው፡፡ አንዳንዶቹ አስተዋይና የበግን ጠባይ ከፍየል ለይተው የሚያውቁ በጎች ‹‹ኸረ እነዚህ ፍየሎች ናቸው ፣ ድምፃቸው ፣ አነጋገራቸውና አኗኗራቸው ያስታውቃል!›› እያሉ ሲሟገቱ ከጥቂቶች በቀር የሚሰማቸው አላገኙም፡፡
አንዳንዶቹ በጎች ‹‹ምን ችግር አለው ፤ አነጋገራቸው እንደ በግ ባይሆንስ? እስከ መቼ እንደ በግ ብቻ እንናገራለን!›› እያሉ ከመቃወማቸውም በላይ በግ የመሰሉትን ፍየሎች ለመምሰል እነርሱም የፍየሎችን አኗኗር ለመኮረጅ ሞከሩ፡፡ የሚያሳዝነው ግን እውነተኛዎቹ በጎች በግ በመሆናቸው ፍየሎቹን ለመምሰል ያደረጉት ጥረት አልተሳካላቸውም፡፡ ሌሎቹ የዋሃን በጎች ደግሞ ምን ችግር አለው? ‹‹የምንመገበው አንድ ዓይነት ምግብ እስከሆነ ድረስ አንድ እኮ ነን!›› ብለው መከራከር ጀመሩ፡፡ ‹‹ኸረ ከመቼ ወዲህ ነው ፍየሎች አንድ የሆንነው?›› ብለው የተቃወሙ በጎች ደግሞ በእነዚህ በፍየሎች በተታለሉ በጎች ጥርስ ውስጥ ገቡ ‹‹አክራሪ ፣ ጽንፈኛና ወግ አጥባቂ በጎች›› የሚል ስያሜም ወጣላቸው፡፡
ይህንን ትርምስ አስቀድሞም ይፈልጉት የነበሩት በግ መሳይ ፍየሎችም ጉዳዩን ማራገብ ጀመሩ፡፡ ‹‹እኛ ለበረታችን ያልሆነው ነገር የለም ፤ እኛ ታማኝ በጎች ነን ፤ ይህቺ በረት ድሮ እንዲህ እንዲህ ነበረች›› ብለው የበረቲቱ መብት ተቆርቋሪዎች ሆኑ፡፡ ይባስ ብለው ድሮ በረቷ የፍየሎች መንጋ እንደነበረች ፣ የምትተዳደረውም በፍየሎች ሕግ እንደነበረ ፤ ከጥቂት ምዕተ ዓመታት ወዲህ በተነሡ በጎች በረቲቱ እንደተበላሸች መወትወት ጀመሩ፡፡ ምንም የማያውቁት በጎች ደነገጡ፡፡ ‹‹ወይኔ በረታችን! ለካ በችግር ላይ ነሽ?›› ብለው በረቲቱን የፍየል በረት ለማድረግ ቆርጠው ተነሡ፡፡ ስለበግነት የሚያነሣን በግ ባገኙት መንገድ ማንቋሸሽም ጀመሩ፡፡
በዚህ መካከል ሌላ ክስተት ተፈጠረ ፤ አንዳንድ ከበጎች ጋር ተቀላቅለው የነበሩ ፍየሎች በይፋ በረቱን ለቅቀው እንደወጡ ተሰማ፡፡ ከወጡ በኋላ ‹‹እውነቱን ተረድተን በግ ከመሆን ፍየል መሆን ይሻላል ብለን ተፀፅተናል ፤ ይህንን እውነት ካወቅን ትንሽ ቆይተናል›› ብለው በአደባባይ ተንሰቅስቀው አለቀሱ፡፡ ሁሉን አይተነዋል ፤ ከእኛ ወዲያ በግነት ለኀሣር አሉ፡፡ በረቱ ውስጥም እያሉ ወሳኝ በጎች እንደነበሩና የበረቱን ጓዳ ጠንቅቀው የሚያውቁ ሊቃውንት እንደሆኑም በዘዴ ጠቆሙ፡፡ አንዳንዶቹም ‹‹የበረቱ ጓዳ›› የሚል መጽሐፍ አዘጋጅተው በተኑ፡፡ ተረባርበው የገዙት በጎቹ ሲሆኑ መልስ ከመስጠት ይልቅ ብዙዎቹ በጎች ተሸማቅቀው ‹‹ጉድ ፣ ጉድ ለካ ይሄ ሁሉ ጉድ አለ?›› ብለው ተንሾካሾኩ፡፡
በዚህ ጊዜ በጎች አሁንም ለሁለት ተከፈሉ፡፡ አስቀድመው ሲቃወሙአቸው የነበሩት በጎች ብዙም ሳይደነቁ ‹‹ከመጀመሪያውስ መች በጎች ነበሩና ነው ፍየል ሆንን የሚሉት ፤ በጎች አለመሆናቸው ይታወቅ ዘንድ ከእኛ ዘንድ ወጡ ፤ በጎች ቢሆኑ ኖሮ ከእኛ ዘንድ ጸንተው በኖሩ ነበር፡፡›› ብለው አስረዱ፡፡ አንዳንድ የዋሃን በጎች ግን ‹‹በግ እገሌ ፍየል ከሆነማ ምን ተረፈን? እንደርሱ ያለ በግ ከየት ይገኛል? ፍየሎችን ያሳፈራቸው እርሱ አልነበረም እንዴ! አይ ይህቺ በረት ምን ቀራት ከእንግዲህ…›› እያሉ ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡ ‹‹ከእንግዲህ ትልቅ ነው ብዬ በግ አልከተልም!›› የሚሉም አልጠፉም ይህን ሲሰሙ አስተዋዮቹ በጎች ‹‹አስቀድሞስ በግ በእረኛ እንጂ በግ በበግ ሲመራ የት አይታችኋል ፤ በሉ ይኼ ትምህርት ይሁናችሁ›› አሏቸው፡፡ከዚህ በተጨማሪ “በግ መስለው የሚኖሩ ፍየሎች አሉ” የሚለው የበጎች አቤቱታ አዝማሚያው ያሰጋቸው አንዳንድ በግ መሰል ፍየሎች የበጎችን ልቅሶ ቀምተው ‘ኧረ ፍየሎች በዙ!’ እያሉ ማስመሰል ጀመሩ።
ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ ደግሞ ትክክለኛው የበጎች በረት የት እንደሆነ ባለማወቅ በጎች ሆነው ሳለ ከፍየሎች መንጋ ጋር የሚንከራተቱ በጎች ጉዳይ ነው፡፡ ወደ ትክክለኛው በረት እንዳይመጡ በበጎቹ በረት አካባቢ የሚታየው ትርምስ የበጎች በረት መሆኑን ስለሸፈነባቸው ተቸገሩ ፣ የብዙዎቹ በጎች ሕይወት ደግሞ የበግ ስለማይመስል የበረቱን በጎ ምስል እንዳይታይ አድርጎታል፡፡ ከፍየል ሌላ የጅብ ፣ የዕባብ ፣ የውሻ ወዘተ ጠባይ የሚያሳዩ በጎች ቁጥር መብዛቱም እነዚህሰ የጠፉ በጎች እንዳይመለሱ እንቅፋት ሆነባቸው፡፡ እረኛው ደግሞ ‹‹ከዚህ በረት ያልሆኑ ሌሎች ብዙ በጎች አሉኝ›› ብሏል፡፡ ከዚህ በረት ውስጥ ያሉ ፍየሎች እንዳሉ ሁሉ ከበረቱ ውጪ ያሉ በጎችም ብዙዎች ናቸው፡፡ ምንም እንኳን እነዚህ የጠፉ በጎች በፍየሎች መካከል ቢሆኑም የበጎች በረት ነገር ሲነሣ ግን በቀላሉ የሚነኩ ፣ልባቸው በቶሎ የሚሰበር ፣ ዕንባ የሚቀድማቸው ናቸው፡፡ የእነዚህ በጎች ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ሆነ፡፡ ‹‹ኸረ ብዙ በጎች እየወጡ ነው!›› እያሉ የሚጮኹም አልታጡም፡፡ አንዳንድ በጎች ደግሞ ለበረቱ የተቆረቆሩ መስሎአቸው ‹‹ይውጡ ፤ ኖረውም አይጠቅሙም! ይላሉ›› እረኛው ግን በጎቹን በበረቱ ለመሰብሰብ ብዙ እንደተሰቃየ ታላላቅ በጎች ታሪክ ጠቅሰው ይናገራሉ፡፡
በዚህ ሁሉ መካከል በረቱ እየፈረሰ ነው፡፡ በጎችም እየኮበለሉ ነው፡፡ ፍየሎችም ሌት ተቀን በረቱን የፍየል መንጋ መስፈሪያ ለማድረግ እየተጉ ነው፡፡ ተስፋ የሚጣልባቸው በጎችም ግማሾቹ ወጣ ብለው ሣር ሲግጡ ውኃ ሲጠጡ ፣ ግማሾቹም በዋዛ በተራ እሰጥ አገባ ተጠምደው ፣ ግማሾቹ በፍየሎች ላለመጠመድ ሲሉ የበረቱን ነገር ወደ ጎን ተዉት፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ እንኳን በረቱን ገብተው ሊታደጉ ሌሎች ትንሽ ሲፍጨረጨሩ ሲያዩ ‹‹አዬ የዚህ በረት ነገር በቀላሉ የሚፈታ እንዳይመስላችሁ… ለማንኛውም መፍጨርጨር ጥሩ ነው!›› ‹‹ይኼን ሠራን ብላችሁ ነው? ወይ አለመብሰል!›› ይሏቸው ጀመር፡፡ ነገር ግን በጎቹ ምንም ባያውቁ በበረቱ ማደጋቸው በራሱ ከመብሰል አልፎ ካልተጠቀሙበት ለማረርም የሚበቃ ጊዜ ነበር፡፡ ይሁንና የጥቂቶቹ በጎች ጥረት ውጤቱ ቶሎ እንዳይታይ ደግሞ ምንም እንኳን ፍየሎች ባይሆኑም እንደ በግ ግን መኖር ያቃታቸው ደካሞች በመሆናቸው አቅም አጠራቸው፡፡ በጎችም ሆነው ፍየሎችን እንዴት እናጥቃ በሚለው ጉዳይ መስማማት አቅቷቸው ሥራውን ሳይጀምሩ የጨረሱ ታካቾችም አሉ፡፡ አንዳንድ በጎች መፍትሔ ለማግኘት “ወደ አንበሳ ሔደን አቤት እንበል” ይላሉ። ሌሎች ብጎች ደግሞ ‘አንበሳ ብዙ አንበሳዊ ጉዳዮች አሉበት ደግሞም አንበሳ የሚፈርደው በጎችንና ፍየሎችን በእኩል ዓይን ተመልክቶ ነው ሲሉ ይሞግታሉ።
የበረቱ ችግር እየከፋ ፣ የፍየሎቹ አካሔድም እየተስፋፋ ቢመጣም አሁንም ግን ዝምታው ሰፍኗል፡፡ ስለ ፍየሎች ጉዳይ እንዲነሣባቸው የማይፈልጉ በጎችም ተፈጥረዋል፡፡ ‹‹ኸረ ፍየሎች እንዲህ እያደረጉ ነው›› የሚል በግ ሲገኝም ‹‹መዓት አታውራ!›› ተብሎ ይገሠፅ ጀመር፡፡ በዕድሜ የገፉ በጎች ደግሞ ‹‹ይህንን ሳላይ በሞትኩ!›› ብለው ያዝኑ ጀመር፡፡ በእርግጥም በዕድሜ የገፉት በጎች ከመቼውም በላይ የተናቁት አሁን ነው፡፡
ፍየሎችን ‹ፍየሎች ናቸው› ብሎ መጥራትም በበጎች ዘንድ ጥላቻን የሚያተርፍ ሆነ፡፡ አንዳንድ በጎች ደግሞ መፍትሔ ያመጡ መስሎአቸው ቢንቀሳቀሱም ፍየልን ፍየል ከማለት ውጪ የበግነትንና የፍየልነትን ልዩነት በሚገባ ማስረዳት ተሳናቸው፡፡ በረቱ የፍየል እንጂ የበግ አልመስል አለ፡፡ አንዳንድ በጎች ጆሮአቸውን ማመን እስኪያቅታቸው የፍየሎች ድምፅ ከበረቱ መሰማቱ እየተለመደ እየተለመደ መጣ፡፡ የሚያስፈራው አዲስ የሚወለዱ ግልገሎች ከልጅነታቸው ጀምሮ ሲሰሙ የሚያድጉት የፍየሎችን ድምፅ በመሆኑ ስለ በግነት እና የበግ ድምፅ ምንም ሳያውቁ የሚያድጉ መሆናቸው ነው፡፡ አንዳንድ በበረቱ ያደጉ በጎች ጭንቀቱን አልቻሉትም፡፡ ‹‹ጆሮዬ ነው ወይስ … እውነት የበረታችን አኗኗር እንደዚህ ነበረ ፤ እውነት ይህቺ በረት ከፍየሎች ጋር አንድ ነበረች? የተሳሳትኩት እኔ ነኝ ወይስ ሌላው?››የሚሉም ነበሩ፡፡ ለማን አቤት እንደሚሉ ጨነቃቸው፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ለእረኛው አመለከቱ፡፡ በጎ ስላደረጉ በጎች መነገሩ ነውር ሆነ፡፡ ፍየሎቹ ስለ እረኛው ብቻ ነው መነገር ያለበት ባዮች ሆኑ፡፡ ስለ እረኛም ግን ስሙን እየጠሩ ከመፎከር በቀር ፍሬ ያለው ነገር አይወጣቸውም፡፡ በዚህ ከቀጠለ ቀስ በቀስ በግ የመሆንና ፍየል የመሆን ልዩነት ጠፍቶ በረቱ መፍረሱ እንደማይቀር አንዳንድ በጎች ይናገራሉ፡፡
በምንባቡ መሠረት የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ
1. ለበረቱ መበጥበጥ ምክንያት የሆኑት እነማን ነበሩ?
2. በግ መስለው የተቀላቀሉት ፍየሎች በምን ይታወቃሉ? (መለያ ጠባያቸው)
3. አንዳንድ የዋሃን በጎች የተሳሳቱት በምን በምን ነበር?
4. በግ ነበርን ብለው የወጡት ፍየሎች መውጣት የማያስደንቀው ለምንድን ነው?
5. ጥሩ ጥሩ በጎች ለምን የበረቱን ችግር ለመፍታት አልቻሉም?
6. ፍየሎችን ‹ፍየሎች› ብሎ መጥራት ለምን ነውር ሆነ?
7. ለበረቱ መልካም ነገርን የሚመኙ በጎች ለምን ተባብረው መሥራት አልቻሉም?
8. ከበረቱ ውጪ ያሉት በጎች ለምን ወደ በረቱ ለመመለስ አልቻሉም?
9. በጎች መመራት ያለባቸው በሌላ በጎች ነው ወይስ በእረኛ?
10. የበረቱን ችግር ለመፍታት ምን መደረግ አለበት (ከጓደኞቻችሁ ጋር ተወያዩበት)
ማሳሰቢያ ፡- ተማሪዎች ይህን ፈተና ከተፈተናችሁ በኋላ የበጎቹንና የፍየሎቹን ገጸባሕርያት እያነሣችሁ አንዳችሁ ለአንዳችሁ ስም እየሰጣችሁ እርስ በእርስ እንድትነቃቀፉ አልተፈቀደላችሁም! የጎበዝ ተማሪ መለያ በረቱ ሰላም የሚሆንበትን መፍትሔ መጠቆም ነው፡፡
መልካም ፈተና.....
(በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ....ምንጭ፡ሐመር የካቲት 2003 ዓ.ም. )Tuesday, 18 March 2014
መጻጉዕ ለምን ትመታኛለህ?
መጻጉዕ ለምን ትመታኛለህ?
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጌታችንከተጠመቀ በኋላ የአይሁድ ፋሲካ ሦስት ጊዜ ተከብሯል፡፡ የመጀመሪያው ፋሲካ ጌታችን ቤተ መቅደሱን ያጸዳበትና በቤተ መቅደስ ሲሸጡሲለውጡ የነበሩትን ያስወጣበት ሲሆን በመጨረሻው ፋሲካም ሰሞን እንዲሁ ለሁለተኛ ጊዜ ቤተ መቅደሱን አንጽቶ ከፋሲካው ማግስት ተሰቅሏል፡፡በሁለቱ ፋሲካዎች መካከል በነበረው ፋሲካ ደግሞ ጌታችን ወደ ቤተ ሳይዳ መጣ፡፡
ቤተ ሳይዳየመጠመቂያው ስፍራ ስም ሲሆን ከአጠገቡ ደግሞ በጎች በር ነበር፡፡ እንደሚታወቀው ዘመነ ኦሪት በግ መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብበት ነበር፡፡ስለዚህ በዚያ በር መሥዋዕት ሆነው የሚቀርቡ በጎች የሚገቡበት ነበር፡፡ በጎቹ ነውር እንደሌለባቸው ማለትም ቀንዳቸው እንዳልከረረ ፣ ጥፍራቸው እንዳልዘረዘረ፣ ጠጉራቸው እንዳላረረ እያገላበጡ የሚጠናበት ፣ የአንድ ዓመት ተባዕት/ወንድ/ መሆናቸው የሚታይበት ሥፍራ ነው፡፡ ይህን መስፈርት አሟልተው ያለፉ በጎች ለመሥዋዕትነት ሲቀርቡ ለዚህ ብቁ ያልሆኑትን ግን ለይተው ፣ በአለንጋ እየገረፉ ያስወጡአቸዋል፡፡
በቤተ ሳይዳየጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያዪቱ ወርዶ ውኃውን አንዳንድ ጊዜ ያናውጥ ነበር፡፡ ይህ መልአክ ‹በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ፣ በበሽታምላይ ሁሉ የተሾመ› የስሙም ትርጓሜ ‹እግዚአብሔር ፈዋሽ ነው› ማለት የሆነ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነበር፡፡መልአኩ ውኆችን ለመቀደስ ፣ ጸሎትን ከሰው ወደ ፈጣሪ ለማድረስ ወደ ውኃው ይወርድ ነበር፡፡ ይህ እንግዲህ ውኃ በራሱ ማዳን ባይቻለውምቅዱሳን መላእክት የነኩት እንደሆነ በረከትና ፈውስ እንደሚሠጥ የሚያስረዳን ነው፡፡ ውኃው ከተነዋወጠ በኋላ ግን መዳን የሚቻለውመጀመሪያ መግባት ሲቻል ነበር፡፡ በዚህ የጠበል ሥፍራ በነበሩ አምስት መመላለሻዎች ‹በሽተኞች ፣ አንካሶች ፣ ዕውሮችና እግራቸው የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር፡፡በተለይ ደግሞ አንካሶች ፣ ዕውሮችና እግራቸው የሰለለ ሰዎች በቁጥር የሚበዙት ከሌላው በሽተኛ በተለየ እነሱ የውኃውን መንቀሳቀስአይተው ለመግባት እንዳይችሉ ወይ ዓይናቸው ማየት አይችልም ፤ ያም ባይሆን መንቀሳቀስ ያቅታቸዋል፡፡ ገብተውም እንኳን ቢሆን ድንገትከእነሱ ቀድሞ የገባ ሰው ካለ እነሱ ስለማይፈወሱ ከውኃው መልሶ የሚያወጣቸውም ሰው ያስፈልጋቸዋል፡፡ አለዚያ ገብተውም አውጪ አጥተውሊቸገሩ ይችላሉ፡፡ ምናልባትም በእንዲህ ዓይነት ችግር ለባሰ ነገር የተዳረገም ሊኖር ይችላል፡፡
ከእነሱቀድሞ የሚድነው እንግዲህ ሁለት ዓይነት ሰው ነው፡፡ አንደኛው በሽታው ለመንቀሳቀስ የማያግደው ሆኖ እያለ የእነሱ ይብሳል ብሎ ሳያዝንየሚገባ ነው፡፡ መቼም ሰው እንኳን ቀድሞ የገባ ሰው ብቻ በሚድንበት ሥፍራ ቀርቶ ፤ በማንኛውም ሰዓት ቢገባ በሚዳንበት የጠበልሥፍራ ‹ከእኔ በሽታ የእገሌ ይብሳል ፤ እስቲ ቅድሚያ ልስጠው› ሲል ብዙ ጊዜ አይታይም፡፡ ስለዚህ እነዚህን ደካሞች ቀድሞ የሚገባበሽተኛ ብዙ ነው፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ወደ መጠመቂያው ሊወረውሩት የሚጠባበቁ ዘመዶች ያሉት ፣ አለዚያም ዘመድ የሚያፈራበት ገንዘብያለው በሽተኛ ደግሞ ሌላው ቀድሞ ወደ መጠመቂያው የሚገባ ነው፡፡
በዚህ ሥፍራለሠላሳ ስምንት ዓመታት ያህል የተኛ በሽተኛ (መጻጉዕ) ነበር፡፡ እንግዲህ ሠላሳ ስምንት ዓመት ማለት የጉልምስና ዕድሜ ነው፡፡መጻጉዕ የመጣው በዐሥር ዓመቱ ነው እንኳን ብንል አሁን አርባ ስምንት ዓመቱ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጌታችን በኋላ ‹የሚብስ እንዳይደርስብህደግመህ ኃጢአትን አትሥራ › ብሎ ስለተናገረ ከመታመሙ በፊት ለዚህ ጽኑ ደዌ የሚዳርግ ኃጢአት ለመሥራት የሚችልበት ዕድሜ ላይ ደርሶአልማለት ነው፡፡ መቼም ክፉ ደግ በማያውቅበት ሕጻንነቱ በድሎ ‹‹የልጅነቱ መተላለፍ ታስቦበት›› ታመመ ብሎ መናገር ይከብዳል፡፡ ብቻይህ ሰው የአንድ ጎልማሳ ዕድሜ ያህል በአልጋ ላይ ሆኖ በቤተ ሳይዳ ተኝቶአል፡፡ ጠበል ሊጠመቅ ሲጠባበቅ በጸጉሩ ሽበት ፣ በግንባሩምልክት አውጥቶአል፡፡
ከሁሉ የሚያሳዝነውደግሞ ይህ ሰው አልጋው ላይ ሆኖ እጅግ ብዙ ሰዎች ሲፈወሱ መመልከቱ ነው፡፡ ከእሱ በኋላ መጥተው ከእሱ በፊት ድነው የሚሔዱ ሰዎችንማየት እንዴት ይከብደው ይሆን? እንደሱ ብዙ ዘመን የቆዩት ሲድኑሲያይ ተስፋው ሊለመልም ይችላል፡፡ በመጡ በአጭር ጊዜ ዘመደ ብዙበመሆናቸው ብቻ የሚድኑ ሰዎችን ሲያይ ግን ልቡ በኀዘን ይሰበራል፡፡ ዓመቱ በረዘመ ቁጥር ተስፋ ቆርጦ ቤተ ሳይዳን ቤቴ ብሎ ከመኖርበስተቀር ምንም የሚታየው ነገር አይኖርም፡፡ እግዚአብሔርን በመከራው ውስጥ ተስፋ እያደረገ ይጽናናል አንዳንል ደግሞ እንደ ጻድቁኢዮብ ወይም እንደ በሽተኛው አልዓዛር ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ግንኙነት የነበረው ቢሆን ኖሮ መቼ ለዚህ በሽታ የሚዳርገው ኃጢአትይሠራ ነበር? ስለዚህ በቃለ እግዚአብሔር ይጽናናል ማለትም ያስቸግራል፡፡ያም ሆነ ይህ ይህ ሰው እጅግ ተሰቃይቶ ነበር፡፡
ጌታችንየዚህን ሰው ችግር ብቻ ሳይሆን ብዙ ዘመን እንደዚህ እንደነበረ ያወቀው ማንም ሳነግረው ነበር፡፡ በሽታውን ከነመንሥኤው አስቀድሞያውቃልና ወደዚህ የብዙ ዓመታት በሽተኛ መጣና ‹ልትድን ትወዳለህን?› አለው፡፡ ጌታችን የሚፈልገው ይህንን ሰው መፈወስ እንጂ የራሱን ማንነት ማሳየት ስላልነበረ‹ላድንህ ትወዳለህን?› አላለውም፡፡ በዚያ ላይ ይህ ሰው የጌታን ማንነት አያውቅም፡፡ ጌታችን ‹ስታምኑብኝ ብቻ ነው የምፈውሳችሁ›የሚል አምላክ አይደለም ፣ ለሁሉ ፀሐይን የሚያወጣ ፣ ለሁሉ ዝናምን የሚያዘንም አምላክ ይህንን ሰውም ለመፈወስ እስኪያምነውም አልጠበቀም፡፡
ይህ በሽተኛ‹ልትድን ትወዳለህን?› ሲባል የሠጠው መልስ እጅግ የሚያስገርም ነው፡፡ እንደሚታወቀው በሽታ አመል ያጠፋል፡፡ በሽታው በቆየ ቁጥርደግሞ መራር ያደርጋል፡፡ ሰዎች በበሽታ ሲፈተኑ በሰው በፈጣሪም ላይ ብዙ የምሬት ንግግር ሊናገሩ ይችላሉ፡፡ ጌታችን ‹ልትድን ትወዳለህን?›ብሎ ሲጠይቀው ‹ታዲያ መዳን ባልፈልግ ጠበል ቦታ ምን አስቀመጠኝ? እያየኸኝ አይደል... › ወዘተ ብሎ ብዙ ያለፈ ንግግር ሊናገርይችል ነበር፡፡ ይህ ሰው ግን ምንም የምሬት እና የቁጣ ቃል አልተናገረም፡፡ ጌታችንም ሲያናግረው በጨዋ ሰው ደንብ ‹ጌታ ሆይ..›ብሎ ነው የመለሰለት፡፡ በዚህ ሁኔታው ትሑት ሊባል ይችላል፡፡
ነገር ግንየመለሰው የተጠየቀውን አይደለም፡፡ ጥያቄው ‹ልትድን ትወዳለህን?› የሚል ከሆነ መልሱ ‹አዎ መዳን እወዳለሁ› አለዚያም ‹አይ አልፈልግም›መሆን ነበረበት፡፡ እሱ ግን ‹ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት።› እንግዲህ የጌታችንን ማንነት ባይረዳውም ጌታችን በወቅቱ የሠላሳ ሁለት ዓመቱነበርና ‹ምናልባት ወደ መጠመቂያው ሊጨምረኝ አስቦ ይሆናል ያም ባይሆን ግን ከተከተሉት ሰዎች አንዱን አደራ ሊልልኝ ይሆናል› ብሎአስቦ ነበር፡፡ ‹ሰው የለኝም› ብሎ የሠላሳ ስምንት ዓመታት ብሶቱን ተናገረ፡፡ ‹ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል› ብሎ እያየ የቀደሙትንሰዎች አስታወሰ፡፡
ጌታችን ‹ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሒድ› አለው፡፡ ባላሰበውባልጠበቀው መንገድ ፈወሰው፡፡ ይህ ሰው ሠላሳ ስምንት ዓመት ሙሉ ሲጠባበቃት የነበረችውን የቤተ ሳይዳ ጠበል ሳያገኝ ፣ በመልአኩመውረድ ሳይሆን በመላእክት ፈጣሪ ቃል ተፈወሰ፡፡ ገባሬ መላእክት ክርስቶስ ራሱ መጥቶ አዳነው፡፡ ይህ ሰው እግዚአብሔር በዚህችጠበል ካልሆነ በቀር በሌላ በምንም መንገድ ያድናል ብሎ አስቦም አልሞም አያውቅም ነበር፡፡ ለመዳን የሚያስፈልገው ምንድን ነው ተብሎቢጠየቅ የሚመልሰው ‹ወደ ውኃው የሚጨምር ሰው እና የቤተ ሳይዳ ውኃ› ብሎ ነበር፡፡ ጌታችን መጻጉዕ ለሠላሳ ስምንት ዓመታት ተስፋያደረጋትን ጠበል ወይም ደግሞ ወደ ጠበሉ የሚጨምሩትን ሰዎች ሳይጠቀም ፈወሰው፡፡ እግዚአብሔር ያለ ጠበልም እንደሚያድን ማመን ካልቻልንእምነታችን ሙሉ አይደለም፡፡ ይህ ሰው ወደ ውኃው ገብቶ ቢድን ኖሮ‹ጌታዬ አዳነኝ› ከማለት ይልቅ ‹‹መዳን ይነሰኝ? ሠላሳ ስምንት ዓመት እኮ ነው የጠበቅኩት...›› እያለ ልፋቱን ያወራርድ ነበርእንጂ ፈጣሪውን አያመሰግንም ነበር፡፡
ጌታችንጠበል ቦታ ያገኘውን ያለ ጠበል ፈወሰው ሲባል መቼም ጠበል መጠመቅ የማይወዱ ወይም በጠበል የማያምኑ ሰዎች ደስ ሊላቸው ይችላል፡፡‹‹እኛስ ምን አልን ጌታ እኮ ይህን በሽተኛ ጠበል ቦታ አግኝቶ እንኳን የፈወሰው ያለ ጠበል ነው›› ብለው ባቀበልናቸው በትር ሊመቱንይፈልጉ ይሆናል፡፡ ሆኖም እዚሁ ዮሐንስ ወንጌል በዘጠነኛው ምዕራፍ ላይ ዕውር ሆኖ የተወለደውን ሰው ጠበል በሌለበት ሥፍራ አግኝቶትእኛ እመት (እምነት) የምንለውን አፈር በምራቁ ለውሶ ከቀባው በኋላ ‹ሒድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ› ብሎ ልኮታል፡፡ ጠበል ምንምየማያስፈልግ ቢሆን ኖሮ ዓይነ ስውሩን ሰው ወደ ወንዝ ወርደህ ተጠመቅ ብሎ አይልከውም ነበር፡፡ ዛሬ ለታመሙ ሰዎች ጠበል ሒዱ ብለንስንመክር ክርስትና ያልገባን ፣ ክርስቶስን የማናውቅ የሚመስለው ይኖራል፡፡ አሁን ባየነው ታሪክ ውስጥ ግን ለበሽተኛው ‹ጠበል ሔደህተጠመቅ› ብሎ የመከረው ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ መፈወስ የሚቻለው ክርስቶስ ጠበል ተጠመቅ ብሎ ከተናገረ ፤ የታመመንመፈወስ የማንችለው እኛ ኃጢአተኞቹ ከንፈር ከመምጠጥ ይልቅ ሔደህ ተጠመቅ ብንል ምን አጥፍተናል? ጌታችን ሲያደርግ ያየነውን ነው፡፡እኔን ምሰሉ ብሎ የለ እንዴ? (ዮሐ. 9፡7)
በእነዚህሁለት ታሪኮች ግን ጌታችን ሲፈልግ በጠበል ሲፈልግ ያለ ጠበል ፤ ሲሻው በምክንያት ሲሻው ያለ ምክንያት፡፡ ሲፈልግ በጠበል ሲፈልግበህክምና ፤ ሲፈልግ በቃሉ ሲፈልግ በዝምታ ፣ ሲፈልግ በቅዱሳን መላእክቱ ሲፈልግ ያለ ቅዱሳን መላእክቱ ማዳን እንደሚቻለው እንረዳለን፡፡
ጌታችንለመጻጉዕ ‹ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሒድ› ብሎ ሲነግረው ወዲውኑ ድኖ አልጋውን ተሸክሞ ሔደ፡፡ እዚህ ላይ አባታችን ቅዱስ ዮሐንስአፈወርቅ እንዳደረገው የበሽተኛውን እምነት እናደንቃለን፡፡ ራሱን መሸከም የማይችለው ይህ በሽተኛ ተነሣና አልጋህን ተሸከም ሲባልአልሳቀም፡፡ ‹እንዴት አድርጌ ነው ደግሞ አልጋ የምሸከመው› ብሎ አልጠየቀም፡፡ በፍጹም እምነት ተነሣና ተሸክሞ ሔደ፡፡ የሠላሳስምንት ዓመት ጓደኛውን ፣ ሰው ሳይኖረው አብራው ኖረችውን ፣ የተሸከመችውን ባለ ውለታው የሆነችዋንአልጋ ተሸክማት አለው - ተሸክሞ ሔደ፡፡
አንድ ሰው እንኳን ለሠላሳ ስምንትዓመታት ይቅርና ለሠላሳ ስምንት ቀናት እንኳን ቢታመም እንደተሻለው ተነሥቶ አልጋ አይሸከመምም፡፡ እስከሚያገግም ድረስ በደንብ መንቀሳቀስአይችልም፡፡ ራሱን ያዞረዋል ፣ ደክመዋል፡፡ የቀረ ሕመም አያጣውም፡፡ መጻጉዕ ግን የተፈወሰው ያለ ቀሪ በሽታ (ያለ ተረፈ ደዌ)ነበር፡፡ ስለዚህ ወዲያው ተነሥቶ አልጋውን እንዲሸከም ነገረው፡፡ መምህር ኤስድሮስ እንዳሉት ያንን የብረት አልጋ ተሸክሞ እየሔደየጌታን ጽንዐ ተአምራት አሳየ፡፡ ጌታችንም ከዛ በሽታ ያዳነው በነጻ መሆኑን በሚያሳይ ሁኔታ ያችን አንዲት ንብረቱንም ተሸክመህሒድ አለው፡፡
መጻጉዕ የተሸከመችህን አልጋ ተሸከምተባለ፡፡ አግዚአብሔር የተሸከሙንን እንድንሸከም የሚፈልግ አምላክ ነው፡፡ ውለታ ሳንረሳ የተሸከሙንን ወላጆቻችንን የተሸከመችንንቤተ ክርስቲያንን ፣ የተሸከመችንን ሀገራችንን እንድንሸከም ይፈልጋል፡፡ በአንዱ ሊቅ ደግሞ ‹ዓለም እንደዚህ ናት ፤ እናት ዓለምአልጋ መጻጉዕን እንደተሸከምኩህ ተሸከመኝ አለችው› ብለው ተቀኝተዋል፡፡ (ይህችን ጽሑፍ በምጽፍበት ወቅት ያለሁት በቅርብ መጽሐፉንማግኘት በማልችልበት ሥፍራ ስለሆነ ቅኔውን ማካተት አልቻልኩም ፤ ዝክረ ሊቃውንት 2 ላይ ነው ያለው)
እዚህ ላይ ጌታችን ቤተ ሳይዳ ከመጣአይቀር ሁሉንም በሽተኛ መፈወስ ሲችል ለምን አንዱን ብቻ ፈውሶ ሔደ? ብለን ማሰባችን አይቀርም፡፡ የበለጠ የሚያሳዝነው ደግሞ ሊቃውንቱእንደጻፉት የቤተ ሳይዳው መጠመቂያ ፈውስ ከዚያ በኋላ ብዙም አልቆየም፡፡ የመልአኩም መውረድ ቆሞአል፡፡ ከዚያ በኋላ በሰባ ዓመተምሕረትም ኢየሩሳሌም መቅደስዋ ፈርሶአል ተመሰቃቅላለች፡፡ ወንጌላዊው ዮሐንስም የዮሐንስ ወንጌልን ሲጽፍ ‹‹ቤተ ሳይዳ የምትባልአንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት።... ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር።... ከማናቸው ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆንነበር።›› ብሎ በኃላፊ ኃላፊ ግሥ /past perfect tense/ ነበር፡፡ ታዲያ ምነው ጌታችን እንዲህ መሆኑን እያወቀ መጻጉዕን ብቻ ፈውሶት ሔደ? ቢባል የፈወሰው እሱን ብቻ አይደለም፡፡እሱን በሥጋ ቢፈውሰውም ተአምራቱን አይተው በማመናቸው በነፍሳቸው የተፈወሱ ይበዛሉ፡፡ ‹ሕሙማነ ሥጋን በተአምራት ሕሙማነ ነፍስንበትምህርት እየፈወሰ› እንዲሉ አበው በዚያ ሥፍራ በሥጋ ታመው በነፍሳቸው አምነው የዳኑ ብዙዎች ናቸው፡፡ የጌታችንና የእርሱ አካልየሆነች የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዋነኛ ሥራ ነፍስን መፈወስ እንጂ ሥጋዊ በሽታን መፈወስ ብቻ አይደለም፡፡ ለዚህ ነው እንጂ ጌታችንሰው ሆኖ ይህችን ምድር በእግሩ ሲረግጥ በሽታ እንዳይኖር ያደርግ ነበር፡፡ ቅዱስ ባስልዮስ ‹በመስቀል ላይ በቆሰልኸው ቁስል ከኃጢአቴቁስል አድነኝ› ብሎ እንደጸለየ እኛም የዘወትር ልመናችን ለሚከፋው ለነፍሳችን በሽታ ነው፡፡
በመጻጉዕ ታሪክ ውስጥ ብዙ ቀሪ ነጥቦችቢኖሩም ሁለት ነገሮችን ብቻ እናንሣና ይህችን አጭር ጽሑፍ እንግታ፡፡ ይህ ሰው ተፈውሶ አልጋውን ተሸክሞ ሲሔድ ሰንበት ለሰው ድኅነትእንደተፈጠረች ያልተረዱ አይሁድ በቁጣ ነደዱ፡፡ ‹‹ሰንበት ነው አልጋህን ልትሸከም አልተፈቀደልህም›› አሉት፡፡ ልብ አድርጉ ይህሰው በቤተ ሳይዳ ሠላሳ ስምንት ዓመታት ሙሉ ሲማቅቅ እንደኖረ የሰውን ገመና አዋቂ ነን ባዮቹ አይሁድ ይቅሩና ቤተ ሳይዳን የረገጠሰው ሁሉ ያውቃል፡፡ ላለፉት ሠላሳ ስምንት ዓመታት ወደዚያች የመጠመቂያ ስፍራ ሲሔዱ ያም ባይሆን በጎች ታጥበው ተመርጠው ወደሚገቡበትወደ በጎች በር ሲያልፉ ይህን በሽተኛ በአልጋው ተጣብቆ ሳዩት አይቀሩም፡፡ አሁን ግን ከአልጋው ተነሥቶ የተሸከመችውን አልጋ ተሸክሞበአደባባይ ሲያዩት የጠየቁትን ጥያቄ ተመልከቱ፡፡ ‹‹እንኳን ለዚህ አበቃህ ፤ ዛሬ መልአክ ወረደ ማለት ነው?›› ‹‹እሰይ ልፋትህንቆጠረልህ!›› ያለው የለም፡፡ የተናገሩት አንድ ዐረፍተ ነገር ነው፡፡ ‹‹ሰንበት ነው አልጋህን ልትሸከም አልተፈቀደልህም›› የሚልብቻ!!! ለእነሱ ድኖ ሠላሳ ስምንት ዓመት የተኛበትን አልጋ ከመሸከሙይልቅ ሰንበት ማፍረሱ ትልቅ ዜና ነው፡፡
መጻጉዕ ‹ያዳነኝ ያ ሰው አልጋህንተሸከም አለኝ› አላቸው፡፡ እስቲ በደንብ አስተውሉ፡፡ እነዚህ ሰዎችይህን በሽተኛ ፈጽሞ አያውቁትም ነበር እንበል፡፡ እንደዛ ከሆነ ‹ያዳነኝ ሰው› ሲላቸው ‹ከምንድን ነው የምትድነው? ምን ሆነህነበር? ከየት ነው የመጣኸው?› ይሉ ነበር፡፡ ነገር ግን ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ መዳኑን ማየት አልፈለጉም እንጂ ማን እንደሆነ ጠንቅቀውያውቁታል፡፡ ከዚያም ‹‹ያዳነኝ ያ ሰው አልጋህን ተሸከም አለኝ›› ሲላቸው ‹‹አልጋህን ተሸክመህ ሒድ ያለህ ሰው ማን ነው?››ብለው ጠየቁት፡፡ እስቲ ጥያቄና መልሱ ውስጥ ያለውን ሽሽት እንመልከት፡፡ ‹‹ያዳነኝ ሰው አልጋህን ተሸከም አለኝ›› ለሚለው መልስተከታዩ ጥያቄ ‹ማን ነው ያዳነህ?› የሚል ነበር፡፡ እነሱ ግን የጌታንየማዳን ሥራ ላለመስማት ጆሮአቸውን ደፍነው ስለነበር ‹አልጋህን ተሸከም ያለህ ማን ነው?› አሉ፡፡ የማዳኑን ሥራ እያዩ ከማመንይልቅ መከራከር ፣ ከማድነቅ ይልቅ የትችት ሰበብ መፈለግ እንግዲህጌታን የሰቀሉ የአይሁድ ጠባይ ነው፡፡
የመጨረሻው ነገር መጻጉዕ ከዚህ በኋላወደ አይሁድ ሄዶ ጌታን መክሰሱና ለጌታ ሞት የመማከራቸው ምክንያት መሆኑ ነው፡፡ ይህ ሰው ‹የሚብስ እንዳይገጥምህ ደግመህ ኃጢአትንአትሥራ› ብሎ ጌታ ቢያሳስበውም አልሰማም፡፡ ጌታ በተያዘበት በምሴተ ሐሙስ ለሊቀ ካህናቱ አግዞ ጌታችንን በጥፊ መታው፡፡ ጌታችንም‹‹ክፉ ተናግሬ እንደሆነ ስለ ክፉ መስክር መልካም ተናግሬ ከሆነ ግን ስለምን ትመታኛለህ?›› አለው፡፡ (ዮሐ.18፡23) ‹‹አልጋህን ተሸክመህ ሒድ ከማለት በቀር ክፉቃል ተናግሬህ ከሆነ መስክርብኝ ፤ የተናገርኩህ መልካም ሆኖ ሳለ ስለምን ትመታኛለህ›› ማለቱ ነበር፡፡ ጌታችን በማግሥቱ ያ ሁሉጅራፍና ግርፋት ሲደርስበት አንድም ጊዜ ‹‹ለምን ትመታኛለህ›› ብሎ አልተናገረም፡፡ የመጻጉዕ ጥፊ ይህን ያህል ዘልቆ የተሰማውለምንድር ነው?
የመጀመሪያው ምክንያት ከቤተ ሳይዳከበጎች በር ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ጌታችን የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ነው፡፡ በበጎች በር አልፎ የመጣውንጹሐ ባሕርይ እንደሆነ ለማስረዳት ነበር፡፡ ለዚህም ንጽሕናው ዋነኛው ምስክር ፈውስን የሠጠው ይህ በሽተኛ ነበር፡፡ እሱ ግን መታው፡፡‹‹በቤተ ሳይዳ ክፉ ቃል ተናግሬህ ከነበር መስክርብኝ› ማለቱ ‹ነውርየሌለብኝ ፣ ለመሥዋዕት የተዘጋጀሁ በግ ነኝ ለምን ትመታኛለህ?› ማለቱ ነበር፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ከሮማውያን ግርፋት በላይለጌታ ዘልቆ የሚሰማው ባዳነው ሰው መመታቱ ስለሆነ ነው፡፡ ውድ አንባቢያን መጻጉዕ ከሠላሳ ስምንት ዓመት በሽታ ብቻ ዳነ ፣ እኛግን የዳንነው ከአምስት ሺህ አምስት መቶ ዓመታት በሽታ ነበር፡፡ ጌታችን እኛን ያስነሣን ከሲኦል አልጋ ነው፡፡ ከሌላው ሰው ይልቅእግዚአብሔር የእኛ ዱላ ይሰማዋል፡፡ ይህም ዱላ ኃጢአታችን ነው፡፡ እግዚአብሔር ዛሬም ድረስ ለእያንዳንዳችን ይጠይቃል፡፡ ‹‹ለምንትመታኛለህ?››
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Tuesday, 11 March 2014
በቅን ሃሳብ ሳይሆኑ ስለ ክርስቶስ ያወራሉ
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
አንድደብዳቤ ከሌላ ሀገር ቤታችን ድረስ በመልእክተኛ እጅ መጣ እንበል፡፡ ደብዳቤው አራት ገጽ ነው፡፡ በዚህ ደብዳቤ ውስጥ ‹በደስታእጸልያለሁ!› ‹ደስ ብሎኛል› ‹ደስታዬን ፈጽሙልኝ› ‹ደስታዬና አክሊሌ› ‹ደስ ይበላችሁ እደግመዋለሁ ደስ ይበላችሁ!› የሚሉ በርካታየደስታ መልእክቶች ተሞልተው ብናይ ‹ይህን ደብዳቤ የጻፈው ሰው እንዴት ቢመቸው ነው?› ብለን መደነቃችን ፣ በደስታውም መደሰታችንአይቀርም፡፡ የፊልጵስዩስ ምእመናን የገጠማቸው ይኼ ነው፡፡ መምህራቸው ቅዱስ ጳውሎስ የላከላቸው ባለ አራት ምዕራፍ መልእክት ደስታየሚለው ቃል ዐሥራ አምስት ጊዜ የተጻፈበት ነበር፡፡ መልእክቱን በደስታ ጀምሮ በደስታ ነበር የጨረሰው፡፡ ከሁሉ የሚያስደንቀው ነገርግን ቅዱስ ጳውሎስ ይህን በደስታ የተሞላ ደብዳቤ የጻፈው እስር ቤት ውስጥ ሆኖ ነበር፡፡
አንድሰው ከእስር ቤት ውስጥ ሆኖ ደብዳቤ የመጻፍ እድል ቢሠጠው ምን ብሎ ይጽፍ ይሆን? ‹‹ምግብ አልተስማማኝም ፣ ተባዩን አልቻልሁትም፣ መኝታው አልተመቸኝም ፣ ፈጣሪዬ ቢገድለኝ ይሻል ነበር›› ይል ይሆን? ለነገሩ ላይልም ይችላል፡፡ የሆዱን በሆዱ ይዞ ‹‹አይዞአችሁአታስቡ ፣ ሁሉም ያልፋል ፣ እኔ ደህና ነኝ›› ይልም ይሆናል፡፡ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ግን በአንድ ደብዳቤ ዐሥራ አምስት ጊዜ ደስይበላችሁ ብሎ ደብዳቤ የሚልክ ይኖራል ብሎ ማሰብ ይከብዳል፡፡ አንድ እስረኛ እንዲህ ብሎ ቢጽፍ እንኳን ቤተሰቦቹ ጤንነቱን መጠራጠርይጀምራሉ፡፡ ‹ተስፋ ቆርጦ ይሆን? በራሱ ምን ክፉ ነገር ሊያደርግ አሰበ? ሊሰናበተን ይሆን› ብለው ሊጨነቁም ይችላሉ፡፡ ሐዋርያውይህን ደብዳቤ የጻፈው ከታሠረ ሦስተኛ ዓመቱ ላይ ነበር፡፡ ስለዚህ ገና የእስር ቤትን ችግር ስላላየ ነው ሊባል አይችልም፡፡ አንዳንዱእስረኛ ደብዳቤ ቢጽፍ ‹ምነው እነ እገሌ መጥተው አልጠየቁኝም ፣ እነ እገሊትስ አብረን በልተን ጠጥተን እንዴት ይረሱኛል?ልውጣ ብቻ› ብሎ ሊያማርር ይችላል፡፡ ደስተኛው ቅዱስ ጳውሎስ ግን ባልጠየቁት ሰዎች አላማረረም፡፡ እንዲያውም በሦስተኛ ዓመት ላይያስታወሱት በመሆኑ ሳይበሳጭ ‹‹ከጊዜ በኋላ ስለ እኔ እንደ ገና ልታስቡ ስለ ጀመራችሁ፥ በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፤ ጊዜ አጣችሁእንጂ፥ ማሰብስ ታስቡ ነበር።›› ብሏል፡፡ (ፊል. 4፡10) የዚህ ሁሉ ደስታው ምክንያት ምን ነበር?
መታሰርለሐዋርያት አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ሁሉም ስለ ወንጌል ታስረዋል ፣ ተግዘዋል ፣ ተገርፈዋል ፣ ሞተዋል፡፡ በሚያስተምሩበት መድረክቃለ ሕይወት ያሰማልን ከመባል ይልቅ የሚጠብቃቸው ዱላና ጅራፍ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ሲደርስባቸው ግን ጠጅ እንደጠጣ ጮማ እንደቆረጠሰው ፊታቸው በርቶ ፣ ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ ስለተገባቸው ደስ ይላቸው ነበር፡፡ የደስታቸውም ምክንያት በሚደርስባቸው መከራ ሳይሆንበሚያገኙት ዋጋ ፣ በሚጠብቃቸው ጸጋ ‹በጌታ› ነበር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በሮም ታስሮ እስር ቤት በየስድስት ሰዓቱ እየተቀያየሩ በፈረቃየሚጠብቁት የንጉሥ ዘበኞች ነበሩ፡፡ ‹‹እስክታሰር ድረስ መከራ እቀበላለሁ ፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም›› ያለው ይህሐዋርያ በፈረቃ የሚጠብቁትን ዘበኞች በፈረቃ ያስተምራቸው ነበር፡፡/2ጢሞ.2፡9/ እስር ቤትን ጉባኤ ቤት ፣ ወህኒውን ቅኔ ማኅሌት ማድረግ የነጳውሎስ የእነሲላስ ዋነኛ ሥራ ነውና ቢታሰርም አልከፋውም፡፡ይልቁንም ከራሱ አልፎ እኛንም ደስ ይበላችሁ አለን፡፡
ቅዱስጳውሎስን ሌላ ያስደሰተው ነገር ቢኖር በውጪ ያለው አገልግሎት አለመታጎሉ ነው፡፡ እውነተኛ መምህር ነውና ከእርሱ መታሰር ይልቅየሚያስከፋው የጉባኤው መፈታት ነው፡፡ ስለዚህ እኔ ከሌለሁ ጥቅሜን ይረዱታል የሚል ምቀኝነት በእርሱ ዘንድ ስለሌለ የትምህርቱ አለመቋረጥደስ አለው፡፡ የሰባኪዎቹ ማንነትና ዓላማ የተለያየ ቢሆንም ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ክርስቶስ ይሰበካል ፤ ስለዚህ ደስ ብሎኛል›› አለ፡፡የቅዱስ ጳውሎስ የደስታ ምክንያቶች ብዙ ናቸውና መጽሐፉን ለአንባቢ በመተው በእርሱ የእስር ቤት ቆይታ ወቅት የነበረውን የሰባኪዎችሁኔታና ዓላማ እንመልከት፡፡
ቅዱስጳውሎስ በመልእክቱ ስላሰሩት ሮማውያን ሳይሆን ‹በጌታ ስላሉቱ ወንድሞች› ወይም ከክርስቲያኖች ወገን ስለሆኑት ክርስቶስን ስለሚሰብኩትአገልጋዮች በሁለት ወገን አድርጎ ተናገረ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ወገኖችበቁጥር የሚበዙት ሲሆኑ ‹ስለ እስራቴ ታምነው የእግዚአብሔርን ቃል እንዲነግሩ ከፊት ይልቅ ይደፍራሉ› ‹ከበጎ ፈቃድ የተነሣ ክርስቶስንይሰብኩታል› ‹ስለ ወንጌል መመከቻ ለማድረግ እንደተሾምኩ አውቀው በፍቅር ይሰብካሉ› በማለት የገለጻቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ወገኖችጳውሎስ የታሰረው ለሹመት ለሽልማት ሳይሆን ለአምላኩ ብሎ እንደሆነ አስበው ‹በሱ ላይ የደረሰ ከደረሰብንም ይድረስብን› ብለው ወስነውእንደ አንበሳ ሳይፈሩ የሚሰብኩ ናቸው፡፡ ስብከታቸውም በበጎ ፈቃደኝነት ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ወንጌል የቆመ ሐዋርያ መሆኑንበማሰብ የእሱን መከራ እያሰቡ በመጽናናት የሚያገለግሉ ቅን አገልጋዮች ናቸው፡፡
ሁለተኛዎቹደግሞ ‹ከቅንአትናከክርክር ፣ በእስራቴ ላይ መከራን ሊያመጡብኝ መስሎአቸው፥ ለወገናቸውየሚጠቅም ፈልገው በቅን አሳብ ሳይሆኑ ስለ ክርስቶስ ያወራሉ።›ብሎ የገለጻቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ወገኖች ስለ ክርስቶስ የሚሰብኩት ለክርስቶስ ካላቸው ፍቅር ሳይሆን ለጳውሎስ ካላቸው ጥላቻ የተነሣነበር፡፡ ‹እሱ ኖረ አልኖረ ወንጌል መቼ ቀረ› እያሉ ለማሳጣት ፣ ወንጌል ያለ ኦሪት ጥምቀት ያለ ግዝረት አትጠቅምም እያሉ ለማሳሳት፣ ሐዋርያውም ‹በእስራቱ ላይ ኀዘን ይጨመርበት ይበሳጭ ፣ ይቃጠል› ብለው ስለ ክርስቶስ ይሰብኩ ነበር፡፡ ክርስቶስን ቢወዱ ኖሮ ስለ ክርስቶስ ታስሮ እየተሰቃየ ያለውን ጳውሎስንም ይወዱነበር፡፡ ለክርስቶስ ያላቸው ፍቅር ልባዊ ስላልሆነና ዓላማቸው ስለ ክርስቶስ መስበክ ስላልነበር ክርስቶስን መስበክን ‹ለቅንዓት፣ ለክርክር ፣ ለጥላቻ› ተጠቀሙበት፡፡
ተመልከቱጳውሎስ ጫማው እንደ ሽንኩርት እስከሚላጥ ዞሮ ያስተማረ ፣ በአይሁድ ዘንድ የነበረውን ዝናና ክብር ፣ እንደሮማዊነቱ የነበረውንስፍራ ስለጌታው ትቶ በፍጹምነት ያገለገለ አባት ነው፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲገደል ቁጭ ብሎ ልብስ ሲጠብቅ የነበረው ይህ ሰው ‹የሚያደርጉትንአያውቁምና ይቅር በላቸው› በሚለው የእስጢፋኖስ ምልጃ ይቅርታ አግኝቶ የአይሁድን ልብስ ከመጠበቅ የክርስቶስ ልብስ የተባሉ ምእመናንንወደመጠበቅ የተሻገረ እረኛ ነው፡፡ (‹አልባሲሁሰ ለክርስቶስ መሃይምናን እሙንቱ› ይላል ብዬ ነው፡፡) ጌታ ‹ምርጥ ዕቃ› ብሎ የጠራውን ቅዱስ ጳውሎስን ጠልቶ ክርስቶስን መስበክእንዴት ይቻላል? ጌታስ ምርጥ ዕቃውን እየወረወሩ እናከብርሃለን ቢሉት እንዴት ይቀበለዋል?እንኳን ምርጥ ዕቃውን አጥሩን እንኳን መነቅነቅ ባለቤቱን መናቅ ነው እንላለን አይደል?እነሱ ግን ይህን አደረጉ፡፡ አጥሩን ነቀነቁ ፤ ባለቤቱንም ናቁ!
የዘመናችንምየስብከት ሁኔታ ይህ ዓይነት ችግር እየከበበው ይመስለኛል፡፡ እርግጥ ነው ዛሬ ቅዱስ ጳውሎስ ያለው እስር ቤት ውስጥ አይደለም፡፡ከወህኒ ብቻ ሳይሆን ከዚህች ዓለም እስር ተፈትቶ ፣ የዓለምን ማሰሪያ ሐምሌ አምስት ቀን በሰይፍ በጣጥሶ ‹ልሔድ ከእርሱ ጋር ልኖርእናፍቃለሁ› ወዳለው ክርስቶስ ሔዷል፡፡ እሱ አይኑር እንጂ በሱ ዘመን የነበረው የሰባኪዎች ዝንባሌ በእኛም ዘመን እየታየ ነው፡፡በዚያ ዘመንየነበሩት ጳውሎስን የሚወዱና ጳውሎስን የማይወዱ ሰባኪዎች ነበሩ፡፡ በእኛ ዘመን ደግሞ ቅዱሳንን የሚወዱና ቅዱሳንን የማይወዱ ሰባኪያንሆኖ ሰፍቶአል፡፡
እናም ስለ ክርስቶስ መናገር ማለት ስለ ቅዱሳን አለመናገር የሚመስላቸው ፣ ከፍ ሲልም የቅዱሳንንስም ማንሳት የሚጠየፉ ‹በፍቅር የማይሰብኩ› ወገኖች እየበረከቱ መጥተዋል፡፡ አንደ ሐዋርያው ስለ ወንጌል የታሰሩ ፣ በእሳት በስለትየተፈተኑ ቅዱሳንን ማሰብም እንደማይፈልጉ በግልጥ መናገርም ጀምረዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ቀድመው ቢወለዱ ኖሮ ሰልፋቸው ከቅዱስ ጳውሎስጋር ከተጣሉት ሰዎች ጋር እንደሚሆን ጥርጥር የለውም፡፡
ቅዱስጳውሎስም ሆነ ሐዋርያቱ የታሰሩት ስለ ክርስቶስ ነበር፡፡ ጌታችን ‹እናንተን የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል› ብሎ ተናግሮላቸዋል፡፡ባለ ሽቱዋ ማርያም የሽቱ ዕቃ ሰብራ በጌታ እግር ሥር ስላፈሰሰች ‹ወንጌል በሚነገርበት ሥፍራ ሁሉ ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆንይነገራል› ብሎ ጌታችን ገድሏ እንዲነገር አዝዞላት ነበር፡፡ (ማቴ.26፡13) ለበደለኛዋ ሴት መታሰቢያዋ ይነገር ብሎ ካዘዘላትበሃሳብዋ ሳይቀር ንጽሕት ስለሆነችው እመቤታችን ቢሰበክ ምኑ ላይ ነው ጥፋቱ? ጠርሙስ ሰብራ ሽቱ ላፈሰሰችው ሴት ታሪኳ ከተነገረ አንገታቸውን ሰብረው ደማቸውን ስላፈሰሱሰማዕታት ቢነገር ምን ይደንቃል? በዝሙት ስለኖረችው ሴት ከተሰበከ ስለ መነኮሳቱ ስለቅዱሳኑ ቢነገርየሚበዛ ይሆን ይሆን? ቅዱሳንን እየጠሉ ክርስቶስን እሰብካለሁ ማለት አይቻልም፡፡ ጌታምእኔን ከጠሩኝ ይበቃል አይልም፡፡ ለሳሙኤል ‹እኔን እንጂ አንተን አልናቁም› እንዳለው ቅዱሳኑን መናቅ እሱን መናቅ ነው፡፡ /1ሳሙ.8:7/
አንዳንዶች‹‹ስለ ቅዱሳንና ስለ ድንግል ማርያም ባለመስበካችን ነው ተቃውሞ የሚበዛብን ፤ እኛ ስለ ክርስቶስ ብቻ ነው የምንሰብከው›› ብለውራሳቸውን እንደ ሐዋርያት ፣ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ቤተ አይሁድ ሊያስመስሉ ይሞክራሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ እንኳን እንዲህ ዓይነትአቀራረብ የለውም፡፡ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ‹እግዚአብሔር ኃያል ነው ፣ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን ፣ እልል በሉ› በሚሉ ቃላትየተሞላ አይደለም፡፡ ስለነ አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ፣ ስለ ኖኅ ሙሴና ሳሙኤል ፣ ስለ ነቢያት ፣ ስለ ሐዋርያት የሚተርከው ክፍልይበዛል፡፡ ጌታችንም ነቢያቱን ቅዱሳኑን እያነሣ አስተምሯል፡፡ ይህ ማለት ስለ እሱ አልተሰበከም ማለት አይደለም፡፡ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻውበሰዎች ሕይወት ውስጥ የምናገኘው የእግዚአብሔርን ቸርነት ፣ ኃያልነትና ምሕረት ነው፡፡ ስሙ ሳይነሣ እንኳን የእሱን ስም ተሸክመውየተጋደሉ የቅዱሳን ሕይወት የእሱን አምላክነት ፍንትው አድርጎ ያሳየናል፡፡ ቅዱሳኑም ያለ እርሱ ምንም ማድረግ እንደማይቻላቸው አስተምረውናል፡፡
ለዘመናችን‹አጽራረ ቅዱሳን› መገለጫ አንድ የሰማሁትን ማሳያ ላስቀምጥ፡፡ በዕለተ ትንሣኤ አንዱ ‹ሰባኪ› ሊያውም በባዕድ ሀገር ላሉ ምዕመናን‹ድንጋዩን ማን ያንከባልልናል?› በሚል ርዕስ ያስተምራል፡፡ ሲያብራራው ‹‹ዛሬ ክርስቶስንእንዳናይ የከለከሉን ብዙ ድንጋዮች አሉ...›› ብሎ ጀመረ፡፡ ‹የከለከሉን ድንጋዮች› ብሎ የተረጎመው ግን ለቅዱሳን ነበር፡፡ የተናገረውክህደት መሆኑ የገባቸው ምእመናንም ፈጽሞ ሳያስታቸው አንገቱን አንቀው ከስፍራው አወረዱት፡፡ በጣም የሚገርመው ግን ‹ድንጋዩን ማንያንከባልልናል› በሚለው ዐረፍተ ነገር ቅዱሳንን ‹ድንጋይ› አድርጎ ሲተረጉም ያላገናዘበው ነገር አለ፡፡ ‹ድንጋዩን ማን ያንከባልልናል›ብለው የተናገሩት ራሳቸው ቅዱሳኑ ነበሩ፡፡ ቅዱሳን ደግሞ ‹እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ› ብለው መንገድ የሚያሳዩንናቸው እንጂ መንገድ የሚዘጉ አይደሉም፡፡ እግዚአብሔር ያሳያችሁ እነዚህ ሰዎች ቅዱሳንን እንደዚህ ጠልተው እንዴት መንግሥቱን ይወርሳሉ? አብርሃምን እየጠሉ እንዴት ከአብርሃም እቅፍ ለመግባት ይታሰባል?(ሉቃ. 16) አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብን አናነሳም እያሉ እንዴት አድርገው ‹‹ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር በመንግሥተ ሰማያት ይቀመጣሉ››? ማቴ. 8፡11 ታቦት ዘዶርየተባለች እመቤታችን ወዳለችበትስ እንዴት መግባት ይቻላቸዋል?
‹‹ስለድንግል ማርያም አንሰብክም›› ባዮቹ ደግሞ የበለጠ ያስደንቃሉ፡፡ እኛ እመቤታችንን እንኳን ላለማመስገን ልናንገራግር ይቅርና በጸያፍአንደበታችን ስምዋን ስለጠራን እንሳቀቃለን፡፡ መጽሐፍ ‹ስለ ጽዮንዝም አልልም› ይላል፡፡ ጽዮን ከተማ ናት ካሉ እንኳን ለከተማ ዝም አልልም ከተባለ ዘጠኝ ወር ስለከተመባት ስለእግዚአብሔር ከተማእንዴት ዝም እንላለን? ‹ወንጌል ነው የምንሰብከው› የሚል ሰው ስለ እመቤታችን እንዴት አልናገርም ይላል? እመቤታችን የኖረችውበኦሪት ነው እንዴ? እስዋ ባትኖር ኖሮ ወንጌል አይጻፍም ነበር፡፡ ስለ እርስዋሳይናገሩ ምን ዓይነት ወንጌል መስበክ ይቻላል? የእርስዋን ስም ሳያነሱ የልደቱን ታሪክ እንዴት መተረክ ይቻላል?የእርስዋን ስም አውጥቶ ስደቱን መናገርስ እንዴት ይሆናል? በቃናው ሰርግ ቤት ያለ እርስዋ ስምና ሚና የተቀዳ ወይንስነበረ? በመስቀል ላይ በደም ተለውሶ እንኳን ስለ እናቱ ተናግሯል፡፡ እኛ ከቤተ መቅደስ የሰማነው ‹ግነዩለእግዚአብሔር ወጸውዑ ሰሞ ፤ እንዘ ኢትፈልጡ እሞ› /መልክአ ቁርባን/ ሲባል ነው (በግጥም ብንተረጉመው ‹ለእግዚአብሔር ተገዙ ፣ ስሙንም ጥሩ ፤ እናቱንም ሳታስቀሩ›እንደማለት ነው /ሳትለዩ/) ስለዚህ እመቤታችንን ሳልጠራ ክርስቶስን እሰብካለሁ የሚሉ ሰዎች ‹‹በቅን አሳብ ሳይሆኑ ስለ ክርስቶስያወራሉ።›› ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ዓይነቶቹን ሰዎች ‹ስለ ክርስቶስ ይሰብካሉ› አይደለም ያለው ‹ያወራሉ› ነው፡፡ ግሡን ይዘንስናራባው ንግግራቸውም ስብከት ሳይሆን ‹‹ወሬ›› ነው ፤ እነርሱም ‹ወሬኞች› ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሰዎች
ስለ ክርስቶስየሚሰብኩት ለክርስቶስ ካላቸው ፍቅር ሳይሆን ለቅዱሳን ካላቸው ጥላቻነው፡፡ ይህም የሃሳባቸው ቅንነት ማጣት ውጤቱን ተራ ወሬ ያደርገዋል፡፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
12/06/2006 ዓ.ም.Sunday, 9 March 2014
ለማይፈጽመው ሰው ትምህርት መጀመር እፍረት ነው፡፡
"ላልተማረ ሰው መጻሕፍትን ማስተማር አፍረት ነው፤ ለስልብ ሰው ከድንግል
ጋር መተኛት አፍረት ነው፤ ጡት ለሌላት ሴት ሕፃን ማሳደግ እፍረት ነው፤ እንጀራ ሳይኖር ማዕድ ማዘጋጀት እፍረት
ነው፤ ለተጠሙ ሰዎች የደረቁ ወንዞችን መጎብኘት እፍረት ነው፤ ፊደሎችን ለማያውቅ መጻሕፍትን መግለጽ እፍረት ነው፤
የቅኝቱን ምት ለማይችሉ መሰንቆ መያዝ እፍረት ነው፤ ለአራሽ ጦር መወርወር፤ ፈረስ መጋለብም እፍረት ነው፤
ለችግረኛ የማያገኘውን መለመን የሚያሳፍር ነው፤ በዘፈን ጨዋታ መካከል ልቅሶ የሚያሳፍር ነው፡፡ በሚያለቅሱ ሰዎች
መካከል በልብስ ማጌጥ እፍረት ነው፤ ለማይፈጽመው ሰው ትምህርት መጀመር እፍረት ነው፡፡"[ መጽሐፈ ምሥጢር፣ የፋሲካ
ማክሰኞ ምንባብ፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ]
በእንተ ቅዱሳት ሥዕላት- ስለ ቅዱሳት ሥዕላት-[ON THE SPIRITUALITY OF ICONS]
Icons have had a place in Christian worship
as early as we can establish.
ጥያቄ አለኝ፡- የቅዱሳን ሥዕል ይናገራል ትላለህ?
ዘማርያም፡- እንዴታ!
ጥያቄ አለኝ፡-ግዕዛን የሌለው (መተንፈስ፣ማሰብ፣መናገር የማይችሉ) ሥዕል ይናገራል ማለት እንደምን ይመቻል; ሐሰት አይሆንም?
ዘማርያም፡- ዳዊት በሚጸልይበት ጊዜ "ሰማያት ይነግራ ስብሐተ እግዚአብሔር- ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፡፡" መዝ.18፡1 ስለሚል ሰማያት በምን አፋቸው ይናገራሉ ትላለህ? አትልም፡፡
ጥያቄ አለኝ፡- እላለሁ እንጂ፡፡
ዘማርያም፡- ግዕዛን የሌላቸው ሰማያት የእግዚአብሔር ምስጋናን ይናገራሉ ማለት እንደምን ይመቻል ሐሰት አይሆንም?
ጥያቄ አለኝ፡- ያስ እንደ ስልቱ ይተረጎማል፤ በሰማያት ያሉ መላእክት እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ ተብሎ፡፡
ዘማርያም፡- ይህም እንደ ስልቱ ይተረጎማል፤ በሥዕሉ ያደረ አምላክ ይናገራል ተብሎ አድገ በለዓም(የበለዓም አህያ)፣ እብነ ቢታንያን(የቢታንያን ድንጋዮችን) ያናገረ አምላክ ሥዕልን ማናገር ያቅተዋል? "ለእመ አርመሙ እሉ እሎንቱ አእባን ይኬልሑ- እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ" ሉቃ. 19፡40፡፡ ዳግመኛስ "ወተዛለፎ ለበለዓም በኃጢኣቱ ዘኢይነብብ አድግ በቃለ እጓለ እመሕያው- ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነቢዩ እብደት አገደ፡፡" 2ኛ.ጴጥ. 2፡16፤ ተናገረ ብሏል፡፡ ነገር ግን ዘይቤውን ሸልቶ መሄድ ነው እንጂ የጠመመውን አቅንቶ የጎደለውን መልቶ መተርጎም የለም ብለህ ስታስተምር ኑረህ ዛሬ በጭንቅ እንደ ስልቱ ይተረጎማል ማለትህ ነገርህ ፈራሽ እንደሆነ በዚህ ይታወቃል፤ የለም ብሎ አለ የሚል መላላሽ ነውና፡፡
ጥያቄ አለኝ፡- ያስ ይሁን ሥዕል ሥራ ይሠራል ትላለህ?
ዘማርያም፡- እንዴታ!
ጥያቄ አለኝ፡- ሥራ ምንድር ነው?
ዘማርያም፡- ልጅ ያስወልዳል፤ ከብት ያረባል፡፡
ጥያቄ አለኝ፡- ሥዕል ልጅ ሊያስወልድ ከብት ሊያረባ እንደምን ይቻለዋል?
ዘማርያም፡- አባግዓ ያዕቆብን(የያዕቆብን በጎች) ተመልከት፤ የተሳለች ዝንጉርጉር በትርን እያዩ ሲወልዱ ሲረቡ እንደ ነበሩ፤ "ያዕቆብም ልብን ለውዝ ኤርሞን ከሚባሉ እንጨቶች እርጥብ በትርን ወስዶ በበትሮቹ ውስጥ ያለው ነጭ እንዲታይ ነጭ ሽመልመሌ አድርጎ ላጣቸው፡፡ የላጣቸውንም በትሮች በጎቹ ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ ውኃ ማጠጫውን ገንዳ ውስጥ በበጎቹ ፊት አኖራቸው በጎቹም ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ ይገAመጁ ነበር፡፡ በጎቹም በትሮቹን አይተው፤ ከመገAምጀታቸው የተነሣ ፀነሱ፤ በጎቹም ሽመልመሌ መሳይና ዝንጉርጉር ነቁጣም ያለበቱን ወለዱ፡፡" ዘፍ. 30፡37-39፡፡ በትሩን እየላጠ ዝንጉርጉርን አድርጎ በውኃው ሲያሳያው በጎቹ ዝንጉርጉርን በትር እያዩ ይወልዱ፣ ይረቡ ነበርና ሥዕለ በትር ከብትን ያረባ ሥዕለ ቅዱሳን እንደምን አይረባ!!!
ጥያቄ አለኝ፡- እውነት ነው እሱ "ለይኩን-ይሁን" ሲለው ይደረጋል!!
ዘማርያም፡- ሥዕለ ቅዱሳንም እሱ ለይኩን-ይሁን ሲለው ሁሉን ያደርጋል፡፡
ጥያቄ አለኝ፡- "ሰአሊ ለነ ሰንበተ ክርስቲያን- በቅዳሴ አትናቴዎስ ላይ ሰንበተ ክርስቲያን(ዕለተ እሑድን) ለምኝልን" ትላላችሁሳ!!
ዘማርያም፡- እንዴታ!! እንላለን፡፡
ጥያቄ አለኝ፡- ግዕዛን(አዕምሮ) የሌላትን ዕለት ለምኚልን ማለት እንደምን ይመቻል; አዕምሮ ማጣት ያስመስል የለም?
ዘማርያም፡- ዳዊት በሚጸልይበት ጊዜ "ዕለት ለዕለት ትጎሥዕ ነቢበ፤ ወሌሊት ለሌሊት ታየድዕ ጥበበ- ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፤ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች፡፡" መዝ. 18፡2 ትል የለምን? አዎን እላለሁ፡፡
ጥያቄ አለኝ፡- ግዕዛን(አዕምሮ) የሌላት ጥበብን ትናገራለች ማለት እንደምን ይመቻል; አዕምሮ ማጣት ያስመስል የለም?
ዘማርያም:- እንደ ስልቱ ይተረጎማል፤ "ሰአሊ ለነ ሰንበተ ክርስቲያን- ሰንበተ ክርስቲያን ዕለተ እሑድ ለምኝልን" ማለትም ዕረፍተ ክርስቲያን የፈጠርህ አምላክ መንፈሳዊ ዕረፍትን ስጠን ተብሎ፡፡ ምነው ጌታችንስ "ነገር ግን እላችኋለሁ፤ በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል፡፡" ማቴ. 11፡22 ሲል ጢሮስና ሲዶና ሲል በጢሮስና በሲዶና የሚኖሩ ሕዝቦችን እንጂ ሐገሩን ነውን; አይደለም!! ወዮልሽ ቅፍርናሆም! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ ሲልስ የቅፍርናሆምንና የቤተ ሳይዳ ሕዝቦችን ክፋትና አለማመን እንጂ መናገር መጋገር የማትችለውን ሐገርን ነውን; አይደለም!!!!
ጥያቄ አለኝ፡- እውነት እሱ!! ግን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እግዚአብሔር በቅዱሳት ሥዕላት ክብሩን የሚገልጽ አብነት ይገኛል?
ዘማርያም፡- እንዴታ!! ቸሩ ፈጣሪያችን ሕያው እግዚአብሔር ታቦትን እንዲሰራ ለነቢዩ ሙሴ ሲያዘው ሁለት የኪሩቤል ሥዕል እንደሚናተፉ አውራ ዶሮዎች አድርጎ እንዲስል ያዘዘ ነው፡፡ በዚህ ሥዕለ ኪሩቤል ላይ ሆኖም እግዚአብሔር ሙሴን ያናግረው አንደ ነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ በዚያውስ ላይ "የእግዚአብሔር ክብርም ከኪሩቤል ወጥቶ በቤቱ መድረክ ላይ ቆመ፤ ቤቱም በደመናው ተሞላ፤ አደባባዩም በእግዚአብሔር ክብር ፀዳል ተሞላ፡፡" ሕዝ. 10፡4፡፡ ይል የለምን; ዳግመኛም "የእግዚአብሔርም ክብር ከቤቱ መድረክ ላይ ወጥቶ በኪሩቤል ላይ ቆመ፡፡ ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ዘረጉ፤ እኔም እያየሁ ከፍ ከፍ አሉ፤ በወጡም ጊዜ መንኮራኩሮች በአጠገባቸው ነበሩ፤ በእግዚአብሔርም ቤት በምሥራቁ በር መግቢያ ቆሙ፤ የእሥራኤልም አምላክ ክብር በላያቸው ላይ ነበረ፡፡" ሕዝ. 10፡18-19 እንዲል፡፡
ጥያቄ አለኝ፡- የቀደምት አበው መጻሕፍት በተለይም የውጭ አኃት አብያተ ክርስቲያናት አበው ስለ ቅዱሳት ሥዕል ምን ይላሉሳ;
ዘማርያም፡-St John of Damascus (ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ) wrote:
“Some people reprove us for honouring images of the Saviour, of the Mother of God
and other holy servants of Christ. But let them think for a moment.
In the beginning God created humanity in his own image. Why ever should we have
such respect for one another, if not because we are made in the image of God?
In Basil’s(የባስልዮስ) words, ‘the honour paid to the image is in reality paid to its prototype,’ that
is to say, to what the image represents. Thus the Jewish people revered the
Tabernacle because that, much more than the rest of creation, was an image of God.
The making and the veneration of images are not a novelty. They are based on a very
ancient tradition.
St Ignatius, bishop of Antioch, (ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ) made the comment:
“He who possesses in truth the word of
Jesus, can hear even its silence.”
Regarding the use of symbols in iconography, one of the church fathers explains:
“There are no words, nor lines which could represent the Kingdom of God, as we
represent and describe our world. Both theology and iconography are faced with a
problem, which is absolutely insoluble –to express by means belonging to the created
world, that which is infinitely above the creature. On this plane, there are no
successes, for the subject itself is beyond comprehension, and no matter how lofty in
content and beautiful an icon may be, it cannot be perfect, just as no word or image
can be perfect. In this sense both theology and iconography are failures. Precisely in
this failure lies the value of both alike; for this value results from the fact that both
theology and iconography reach the limit of human possibilities and prove
insufficient. Therefore the methods used by iconography for pointing to the Kingdom
of God, can only be figurative and symbolical, like the language of the parables in the
Holy Scriptures.”
In the Coptic Church, icons follow certain symbolism that carries a theological
message.
St Ambrose(ቅዱስ አምብሮስ) writes of her:
“The life of Mary shines forth as from a mirror, all the beauty and chastity and the
pattern of every virtue.”
Thus, it is not surprising that St Jacob of Sarug(ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ) expressed:
“How could I paint the picture of this marvellous, beautiful one with ordinary
colour? Too exalted and too glorious is the image of her beauty!”
Mary is found in many icons, most frequently holding Christ. And although the icons have numerous variations, she always has one hand which motions towards her son – the action that sums up her entire life to the present day.
Thus, in conclusion, icons in the Orthodox tradition are not to be taken as pieces of
artistic device, but rather, as windows or doors into spiritual world. They are designed
to enhance the spiritual life of the believer through emulating the virtues of the icon’s
prototype. And therefore, icons can be a blessing in our lives if we use them in a
spiritual way.
እግዚአብሔር ለኹላችንም ትሑት ስብእና ቅን ሕሊና አስተዋይ ልቡና ይስጠን፡፡ አሜን፡፡
ስምዓት(ምንጭ)- መጽሐፈ ጥበብ፤ ዘአስተጋብእዎ አኀው ማኅበረ ቢዘን፤ ገጽ.49-51.
- “THE SPIRITUALITY OF ICONS”, By His Grace Bishop Daniel

Subscribe to:
Posts (Atom)